ሃምሳ ሦስተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የገንዘብ፣ ዕቅድ እና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሮች ጉባዔ አጀንዳ ወቅታዊ እና ተገቢ ነው፡፡ በዓለማችን እየጨመረ ከመጣው ተፈጥሯዊ እና ሰብአዊ ነውጥ ጋር በተያያዘ፣ ፈጠራ የታከለባቸው ምላሾች ያስፈልጉናል። አፍሪካ የኮቪድ19ኝን ቀውስ ተጋፍጣ መፍትሔዎችን ለመቅረጽ እና ተግባራዊ ለማድረግ ያሳየችውን ዐቅም እና ዝግጁነት የሚደነቅ ነው፡፡ ቀጥለን በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በአየር ንብረት ለውጥ ተኮር ኢኮኖሚ እና ተቋማዊ ማሕቀፎችን በማብቃት ላይ ልናተኩር ይገባል። ይህንንም እውን ማድረግ እንደሚቻል በሀገራችን ያስጀመርናቸው ምዕራፎች ያመላክታሉ። አህጉራችን የዓለም አቀፍ ምጣኔ ሀብት ዐምድ መሆኗ የማይቀር ነው!
How to Watch Stories from Instagram