በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ከተጠጉ የሶሪያ ስደተኛ ወንድምና እኅቶቼ ጋር የረመዳን ኢፍጣር ማዕድን ተጋርተናል። ይህ አጋጣሚ ገና በኢስላም ማለዳ ቀናት አያቶቻችን የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የቅርብ ዘመዶችና ሶሃቦችን ተቀብለው ያስተናገዱበትን አንፀባራቂ ታሪክ የሚያስታውሰን ነው።

በዚህ ድንቅና ውብ ታሪካችን እንደምኮራው ሁሉ፤ ሕዝባችን በተለይም በወጣቱ ትውልድ ውስጥ ለተቸገሩ፣ ለተሰደዱና ጎዳና ላይ ለወደቁ የሰብአዊነትና የእምነት ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ትኩረት እንዲሰጡ እንሻለን። ይህ ሁኔታ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዛሬም ወደፊትም ከሙስሊም ሀገራትና ሕዝቦች ጋር በወዳጅነት፣ በፍቅርና በሰላም ለመኖር ያለንን ጠንካራ ፍላጎትና እምነት የሚያጸና ነው።

‎لقد شاركنا اليوم بماءدة الإفطار الرمضانية إخواننا وأخواتنا من اللاجئين السوريين المتواجدين في أثيوبيا. ويعيد هذا الحدث الي أذهاننا وذاكرتنا الجماعية نحن الأحباش كيف إستقبل أجدادنا وأمجادنا المهاجرين من الصحابة الأجلاء وأقرباء النبي سيدنا محمد (صلعم) في فجر الإسلام.

‎وكما نفتخر ونعتز بذالك التاريخ الجلي نكرس لذى شعبنا وخاصة جيل الشباب ثقافة الإهتمام بالمهاجررين، والمسكين وأبناء السبيل من إخواننا وأخواتنا في الإيمان والإنسانية. وتصب كل هذه الظواهر في الحاضر والماضي في رغبتنا المخلصة والصادقة بأن نعيش مع أخواننا من الشعوب الإسلامية بالوئام والمحبة والسلام دائما وأبدا.
Top 5 Best Zoom Cameras