ድል ያለ መሥዋዕትነት አይገኝም። ጀግናው ሠራዊታችን የሀገራችንን ክብር፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት የሚያስከብረው የላብና የደም ዋጋ ከፍሎ ነው። ይሄንን ተመን የማይገኝለት ዋጋ ሲከፍል ደግሞ ሕዝብ እና መንግሥት ከጎኑ መቆም አለባቸው።
እንደ ወታደር ዓለሚቱ አምባ ያሉ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የተጎዱ የሠራዊት አባላት ለጀግንነታቸው የሚመጥን ክብካቤና ድጋፍ እንዲያገኙ እየሠራን ነው። የሕክምናና የሰው ሠራሽ አካል ድጋፍ ማድረጊያ ማዕከላትን እያጠናከርን ነው። ማኅበራዊ ሕይወታቸውን ለመደገፍ የሚያስችል ሥራም እየሠራን ነው። ኢትዮጵያ ለእነርሱ የማትሆነው የለም።
External Redirect | Bukkit Forums