ብዙዎቹ የሙያ ዘርፎች ፍላጎትና ተሰጥኦ ይሻሉ። ለውትድርና ግን ቀዳሚው ጉዳይ ጥልቅ የሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት ነው። እንደ ሌላው ሙያ ውትድርና እውቀትና ጉልበት ብቻ አይፈልግም፤ ደምና አጥንትን ለመገበር ዝግጁ መሆን ጭምር እንጂ። ባንዴራችን የሚውለበለበው ከሁሉ በላይ ከጀግና ወታደሮቻችን በሚፈልቀው ትንፋሽ ነው። ታከተኝ ሳይሉ ሀገርን ከማገልገል፣ ሳይሰስቱ ፍቅርን ከመስጠት፣ በመርህ ኖሮ ለመርህ ከመሰዋት የበለጠ አኩሪ ገድል የለም። ሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ “የወታደር ልጅ ነኝ” ብላ ስትናገር እጅግ በኩራት ነው። ወታደር መሆን ደግሞ ኩራቱ የትናየት ከፍ እንደሚል አስቡት፡፡ ሳይሰስቱ ሀገር ማፍቀርንና ሳይታክቱ ሕዝብ ማገልገልን ከወታደሮቻችን እንማር!
The Benefits of Using a YT Audio to MP3 Converter