Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
114K subscribers
5.1K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
ከኢስላሚክ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ አል ጃስር ጋር በመገናኘቴ ደስተኛ ነኝ። በኢትዮጵያ ላሉ አዳዲስ እንቅስቃሴዎች የተለያየ ድጋፍ በመፈለግ ዙሪያ ተወያይተናል።

Pleased to meet with the President of the Islamic Development Bank Dr Muhammad. Al Jasser. We’ve discussed on exploring support for the new momentum in Ethiopia in various areas.
Statement at the 36th Ordinary Session of the Assembly of the Union
የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ከሆነው ከወንድሜ ዶ/ር አኪንዉሚ አድሲና ጋር መገናኘት ሁሌም አስደሳች ነው። የልማት ባንኩ ለግብርና ክፍለ ኢኮኖሚያችን በተለይ ለስንዴ ምርታማነት ጥረታችን እና ለሌሎች ቁልፍ ምርቶቻችን የሚያደርገው ያልተቋረጠ ድጋፍ ወሳኝ ነው።

Always good to meet my brother Dr Akinwumi Adesina, President of the African Development Bank. AFDBs continued support to our agricultural sector is critical particularly in our wheat productivity endeavors as well as other key produce.
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደኅና መጡ:: ከአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ጎን ለጎን ባደረግነው የሁለትዮሽ ውይይት በሰላም ስምምነቱ አተገባበር እንዲሁም የመንግሥታቱ ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ የበለጠ ማሳደግ በሚቻልበት ዙሪያ ተወያይተናል።

I welcome UNSG Antonio Guterres to #Ethiopia. We’ve discussed progress on the peace agreement during our bilateral meeting on the sidelines of the #AUSummit and how to further enhance the UNs support to Ethiopia.
ከአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ጎን ለጎን ከፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ከፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሼኬዲ፣ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ እና ከፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳዪሺሚዬ ጋር ተገናኝቻለሁ። በቀጣናዊ እና የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።

On the sidelines of the #AUSummit I have also met with President Paul Kagame, President Felix Tshisekedi, President Hassan Sheikh Mohamud and President Evariste Ndayishimiye during which we discussed regional and issues of mutual interest.
ከቻርለስ ሚሼል ጋር በአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ወቅት ስለተገናኘን ደስ ብሎኛል። በሰላም ስምምነቱ ላይ በነበረው የመንግሥት ሚና፣ በልማት ሥራዎች እና በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ኅብረት ግንኙነት ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገናል።

Good to meet with Charles Michel on the sidelines of the #AUSummit. Our discussions focused on progress by the government on the peace agreement, development endeavors and Ethiopia-EU relations.
ከታንዛኒያ ፕሬዝዳንት፣ ከሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬትስ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል።

I also held bilateral meeting with the President of Tanzania, the Vice President of Libyan Presidential Council as well as the State Minister of the UAE.
The Art of Tweeting: Crafting Engaging and Shareable Content on Twitter