Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
114K subscribers
5.11K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
እንኳን ለ1496 ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከሚኒስትር እና ሚኒስትር ዴኤታዎች ጋር በስልጠና ማጠቃለያ።
Ministiroonnifi deetaawwan ministirootaa waliin xumura leenjii irratti
በታማኝነት መትጋት ለትውልድ ማሰብን፣ ሀገርን ለማቅናት መነሣትን ያሳያል። ዛሬ ለእውቅና የበቃችሁ ግብር ከፋዮችን ሀገር ታመሰግናችኋለች። ባለፈው ዓመት በዚሁ መድረክ ታማኝ ግብር ከፋዮች ሥራችሁን ስትሰሩ ሌብነትንም እንድትዋጉ ጥሪ አቅርቤ ነበረ። ጥሪውን ለተቀበሉት ቆራጦች ልዩ እውቅና ሰጥተናል። በሚቀጥሉት ዓመታትም ሀገርና ትውልድን አክብራችሁና አስቀድማችሁ አርዓያነታችሁን ወደ ሌሎች እንድታጋቡ አደራ እላችኋለሁ።

Amanamummaadhaan cimanii hojjechuun dhalootaaf yaaduufi biyya olqabuuf ka'uu agarsiisa. Kanfaltoota gibiraa har'a beekamtii argachuuf geessan Itoophiyaan isin galateeffatti. Bara darbe waltajjiidhuma akkanaarratti kanfaltoonni gibiraa amanamoon wayita hojii keessan hojjetan hattummaarratti akka qabsooftan waamicha dhiyeesseen ture. Kutattoota waamichichaaf deebii kennaniif beekamtii addaa kennineerra. Waggoota dhufanittis biyyaafi dhaloota kabajjaniifi dursa kennitaniifi fakkeenyummaa keessan warra kaaniin akka geessan adaraan isiniin jedha.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በታማኝነት መትጋት
Amanamummaadhaan cimanii hojjechuu
Diligence in being faithful
ዕንቅፋትና ፈተናዎቻችን አሰናክለው አያስቀሩንም። እንዲያውም የመሸጋገሪያ ድልድዮች ሆነው ያገለግሉናል። ዓለማችን ላይ ቁልፍ ግኝቶች የተገኙት፣ አስደማሚ ቴክኖሎጂዎች የተሠሩትና ችግር ፈቺ መፍትሔዎች የተፈጠሩት በፈተና ጊዜ ነው። በፈተና ጊዜ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዕንቅፋትን ወደ ዕድል ለመለወጥ በሚነሡ ብርቱዎች ትጋት እንደሆነ የብዙ ሀገራት የሥልጣኔ ታሪክ ያስተምረናል። ሁላችንም ተረባርበን ይኼንን ወቅት ለመልካም ለውጥ ከተጠቀምንበት ያለ ጥርጥር መጪው ዘመን ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን የሚሆንበት ጊዜ ነው። በምድር በሰማይ ብለን፣ ኃይላችንን አስተባብረን፣ ክፍተታችንን ሞልተን፣ ለአንድ ዓላማ ተሰልፈን፣ በኢትዮጵያ ጠላቶች ፍጻሜ ላይ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናበሥራለን።

Gufuufi qorumsi gufachiisanii nu hin hambisani. Hinumaayyuu riqichoota cehumsaa ta'anii nutajaajilu. Addunyaa keenyarratti argannoowwan ijoo ta'an kan argaman, teknooloojiiwwan dinqisiisoon kan hojjetamaniifi fuurmaatawwan rakkoo hiikan kan uumaman yeroo qorumsaattidha. Yeroo qorumsaa qofaatti utuu hin ta'iin cimina warra jajjaboo gufuu gara carraatti jijjiiruuf ka'aniin akka ta'e seenaan nubarsiisa. Yoo hundi keenya tumsinee yeroo kana jijjiirama gaariif itti fayyadamne, barri dhufu shakkii malee Itoophiyaaf badhaadhinni gama hundaa kan itti dhugoomudha. Samiifi lafarratti jennee, humna keenya waltaasifnee, qaawwa keenya duuchinee, kaayyoo tokkoof hiriirree, xumura diinota Itoophiyaarratti badhaadhina Itoophiyaa ni labsina.
የመረረውን ትግል ታግለን፣ ጣፋጩን ድል እናጣጥማለን።

የሽብር ቡድኑ ሕወሓት፣ ያሳደገች እናቱ ላይ የመከራ ቋጥኝ እንደሚጭን ክፉ ልጅ፣ አሁንም ለኢትዮጵያ የመከራ ቋት መሆኑን ቀጥሏል። በጥላቻ ፕሮፓጋንዳው አነሳስቶ የሰበሰባቸውን ኃይሎች ይዞ በአራት ግንባሮች ተኩስ ከፍቶ ሀገር የማፍረስ ተግባሩን ገፍቶበታል። መከላከያ ሠራዊታችና የእናት ሀገር ጥቃት ግድ የሚለው የወገን ጦር በአንድነት ሆነው ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን ጥቃት ለመመከት በሁሉም ግንባሮች ተሰልፏል። ጠላት የመጨረሻ አቅሙን አሟጥጦ ለማጥቃት የሚያደርገውን ጥረት ሠራዊታችን በምድርና በአየር እየታገዘ እንዳይነሳ አድርጎ እየሰበረው ይገኛል።

በሦስቱ ግንባሮች እንደማያዋጣው የተገነዘበው አሸባሪው ሕወሐት፣ ሰሞኑን ያለ የሌለ ኃይሉን ወደ ወሎ ግንባር አምጥቷል። ለበቀለበት ሕዝብ ጨምሮ ለማንም ርህራሄ የሌለው ቡድኑ በዘመቻው ከ12 ዓመት ሕጻን እስከ 65 ዓመት አዛውንት ያገኘውን ሁሉ ሰብስቦ አዝምቷል። ይኼን ሲያደርግ ዓላማው ሁለት ነው። አንድም ያሰማራው ኃይል ጨርሶ ተስፋ እንዳይቆርጥና ሞራሉ እንዲያንሰራራ ለማድረግ በወሎ በኩል ድል የማግኘት ምኞት አድሮበታል። ሁለትም በቅርቡ አየር ኃይላችን ጥቃት ሰንዝሮ ያወደመበትን ከባድ መሣሪያ ከመከላከያ ሠራዊት ማርኮ ለመተካት በማሰብ የሞት ሽረት ትግል አድርጓል። ለድል ቋምጦ መጥቶ ጠላት በወሎው ግንባር ሰፊ ቁጥር ያለው ኃይሉን ያጣ ሲሆን፣ ጀግናው ሠራዊታችን በሁሉም መስክ መሥዋዕትነትን ከፍሎ እየተጋደለ ነው።

በቀጣይ ጊዜያትም ጠላት የተረፈውን ኃይል አሰባስቦ ተመሳሳይ ጥቃቶችን መሠንዘሩ አይቀርም። የጠላት የጥንካሬ ምንጭ የእኛ ድክመትና መዘናጋት እንደሆነ አውቀን ነቅተንና ተባብረን ልንጠብቀው ይገባል። ብዛታችን ጥንካሬ የሚሆነው ተግባብተን በአንድነት ስንቆም ነው። መነጣጠላችን ለጠላት ይመቻል። በሚነዛው ፕሮፓጋንዳ መረበሻችን እሱን ካልሆነ በቀር ማንንም አይጠቅምም። እርስ በእርሳችን መደማመጥና መተባበር ከቻልን መፍረክረክ የጀመረ የጠላት ጉልበት ይንበረከካል፤ እንደ ክር የሰለለ ምኞቱም ይጨነግፋል። ሀገር ለማጥፋት የመጣ መንጋ ሀገር ለማዳን የተነሣን ኃይል ይረብሸው ይሆናል፣ ሊያሸንፈው ግን አይችልም።

ሥራችንን በተናበበና በተቀናጀ መልኩ ከማከናወን ባለፈ፣ በመካከላችን ሆኖ ለጠላት የሚሠራውን የሕወሐት ወኪል በንቃት መከታተል ያስፈልጋል። ለዘመናት ከጠላት ጋር የጥቅም ትስስር የፈጠሩ ሰዎች ዛሬም በጉያችን ሆነው የጠላትን ምኞት ከዳር ለማድረስ ደፋ ቀና ይላሉ። ስለዚህ ሁሉም ዜጋ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን የጠላት ወኪሎችን ማጋለጥ ይገባል።

በሚገጥመን ፈተና ሳንረበሽ ሁላችንም የበኩላችንን ሚና ከተጫወትን ፈተናችን የሚወገድበት ጊዜው ሩቅ አይሆንም። በተቃራኒው ተግባሩን ትተን የምንጠይቅ ብቻ ከሆንን የድላችን እድሜ ይዘገያል። ሀገርን ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነት የጥቂቶች ሳይሆን የሁላችንም ነው። እያንዳንዱ ዜጋ ከእኔ ምን ይጠበቃል? እኔ ምን እያደረኩ ነው? ማለት አለበት። የእሱ ደህንነት እንዲጠበቅ፣ እሱ ሰላም ውሎ እንዲያደር፣ ሠርቶ እንዲያተርፍ ለእሱ ሲሉ ሌሎች የሚሰውበት ምክንያት የለም። ሁሉም ከወዙ ጨልፎ፣ ከደሙ ቀንሶና ከአጥንቱ ፈልጦ በሚያተበረክተው አስተዋጽኦ ነው ሀገር ነፍስ ኖሯት፣ በሁለት እግሯ የምትቆመው። ለኢትዮጵያ የመሞት ግዴታ የሁላችንም እንጂ፣ የተለየ ሞት እንዲሞት የሚጠበቅበት የተለየ አካል የለም።

ስለዚህ ሕዝባችን የክት ጉዳዩን ለጊዜው አቆይቶ፣ ለማጥፋት የመጣውን አሸባሪውን ሕወሓት ለመመከት፣ ለመቀልበስና ለመቅበር ማናቸውንም መሣሪያና ዐቅም ይዞ፣ በሕጋዊ አደረጃጀት መዝመት አለበት። ይህ ታላቅ ሕዝብ ታላላቅ ታሪካዊ ፈተናዎችን ድል የነሳው ዳር ቆሞ በማየት ወይም በጥቂት ድል ረክቶ በመቀመጥ አይደለም። የተሰነዘሩብንን ጥቃቶች ያሸነፍነው በአንድነት ለሀገራችን ጸንተን ዘብ በመቆም ነው።

የቀደምት አያቶቻችንን የጀግንነት ፈለግ በመከተል ማንኛውንም እኩይ ተግባር ማክሸፍ እንደምንችል ማመን አለብን። አሁን የገጠሙን ፈተናዎች የማይታለፉ እና ውስብስብ ሊመስሉ ይችላሉ። ነገር ግን ቀደምቶቻችን ካዩት መከራ የሚከብዱ አይደሉም። ቁልፉ ጉዳይ በአንድነት መቆም፣ በጥሞና መደማመጥ እና ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ ናቸው። ይኼን ካደረግን የቀደመው ትውልድ ሀገርን ጠብቆ ወደ እኛ ማስተላለፍ እንደቻለው፣ እኛም ኢትዮጵያን አስከብረን ለቀጣዩ ትውልድ እናወርሳለን። ጫጫታና ማወናበዱ ቢበረታም ዛሬን በትኩረት እንድንቆም፣ ያለ አንዳች ማመንታት ኢትዮጵያን በአንድነት ከጥቃት እንድንከላከላት ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ይኼ ጊዜ ችግሮች ተደራርበው የመጡበት የፈተና ጊዜ ነው። ፈተናው እስኪያልፍ ሁሉም ሰው መፈተኑ አይቀርም። ችግሮቻችን አፋጣኝ መፍትሄ አግኝተው ወደ መደበኛ ኑሮ እስክንመስ ሁላችንም አኗኗራችንን ለፈተና ጊዜ እንዲስማማ አድርገን መቆየት አለብን። እንደ ሰላሙ ጊዜ ነገሮች አልጋ በአልጋ እንዲሆኑ መጠበቅ የሰላሙን ጊዜ ያርቀዋል እንጂ ፈጽሞ አያቀርበውም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀውም የመከራውን ጊዜ ለማሳጠርና የመፍትሔውን ጊዜ ለማቅረብ ነው። ስለዚህ ዜጎች ወቅቱ እንደሚጠይቀው በመሆን፣ አዋጁ የሚያዝዛቸውን መመሪያዎች በማክበር፣ የሕግ አስከባሪ አካላት ሥራቸውን በቅልጥፍና እንዲያከናውኑ በመተባበር እና አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ሁሉም የበኩሉም ሚና እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ ለተሠዉ ጀግኖቻችን!!

ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር ናት፡፡ ልባም ልጆችዋ አጥር ሆነው የጋረዷት፣ ዋጋ ከፍለው ያደመቋት፣ ተቆጥሮ በማያልቅ መሥዋዕትነት ታፍራና ተከብራ የኖረች ሀገር ናት፡፡ የሩቁ ቢዘነጋን እንኳን፣ አምና ጥቅምት 24 ግፍ የተፈጸመባቸው ጀግኖቻችን ታሪክ ፈጽሞ የሚረሳ አይደለም፡፡ እያንዳንዳችን የጀግኖቹ ዕዳ አለብን፡፡ ዛሬ የቆምነው ለእኛ ሲሉ የግፍ ጽዋን በተጎነጩ ጀግኖቻችን አጥንት ላይ ነው፡፡ እነዚያ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች “ከወገኔ በፊት እኔ ልቅደም” ብለው ደማቸውን ለአፈር፣ ሥጋቸውን ለአሞራ ባይሰጡ ኖሮ የዛሬው ቀን ዛሬን ባልመሰለ ነበር፡፡

የሰሜን ዕዝ ሠራዊት የተደራጀው ከአንድ አካባቢ አልነበረም፡፡ አማራና ኦሮሞው፣ ሲዳማና ወላይታው፣ አፋርና ጋምቤላው፣ ጉራጌና ሐድያው ከሁሉም ብሔር ተውጣጥቶ ሀገር እንዲጠብቅ የተደራጀ ሠራዊት ነበር፡፡ ሀገሬን ብሎ ለሃያ ዓመታት ከቤቱና ካሳደገው ቀዬ ተነጥሎ ዱር እያደረ ድንበር ሲጠብቅ ኖሯል፡፡ ሠራዊቱ ለትግራይ ክልልና ለሕዝቡ ከደግነት ውጭ ክፉ ሆኖ አያውቅም። ጠላት ሲመጣ የሚመክት፣ አዝመራ ሲደርስ የሚያጭድ፣ በማኅበረሰባዊ ተግባራት ላይ የሚካፈል ነበር። በደምና በላቡ ለከፈለው ደግነት በምላሹ ከሽብር ቡድኑ ሕወሐት የተቀበለው ክህደት ነው።

ኢትዮጵያን ለመውረር የመጡ ጠላቶች እንደ ሽብር ቡድኑ ዋነኛ የጦር ቤዛችንን በመደብደብ አልጀመሩም፡፡ ዋና ዋና መኮንኖችን በመግደልና ከባድ መሣሪያዎቻችንን ዘርፈው አልተነሡም። የጦርነት ቅዱስ ባይኖርም ለጭካኔም ልክ አለው። በሽብር ቡድኑ ልክ ኢትዮጵያ ላይ የጨከነ የለም፡፡ ጥቅምት 24 ሠራዊቱ ላይ የክህደት ጥቃት ሲፈጸም የሞቱት እነዚያ ጀግኖች ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ እንደመሆናቸው የተፈጸመባቸው ግፍ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመ ግፍ ነው።

የሽብር ቡድኑ በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመው ጥቃት መሣሪያ ለመዝረፍ ብቻ የተደረገ ተራ ጥቃት አልነበረም፡፡ በተንኮል የተቀመመና በክፋት የሞላ መሆኑ የተለየ ያደርገዋል፡፡ የገዛ ጓዶቹን አስኮብልሎ በተኛበት ከመግደል ባለፈ ከሬሳው ላይ ልብሱን ገፍፎ የአውሬ ቀለብ እንዲሆን እርቃኑን ሜዳ ላይ ጥሎታል። ይኼን ሲያደርግ የሽብር ቡድኑ ዓላማ ሁለት ነው፡፡ አንደኛ ሠራዊቱ በሐፍረት በትር እየተቀጣ ሞራሉ እንዲላሽቅና የአቅመ ቢስነት ስሜት እንዲሰማው፡፡ ሁለተኛ ሠራዊቱ እርስ በእርስ እንዳይተማመንና “ክፉና ደጉን አብሮ ከተካፈሉኝ ጓዶቼ እንደዚህ ዓይነት ነውር ዛሬ ከተፈጸመብኝ ነገስ?” ብሎ እንዲጠራጠር ለማድረግ ታስቦ ነበር፡፡ ዳሩ ግን ሠራዊቱ እንደተጠበቀው አልሆነም፡፡

የወንድሞቹ ደም በከንቱ መፍሰስ ያንገበገበው ሠራዊት በፍጥነት ራሱን አደራጅቶ በሦስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የሽብር ቡድኑ ያደራጀውን ኃይል ወደ በርሃ እንዲበተን ማድረግ ችሏል፡፡ የቡድኑን ቁንጮ አመራሮች አብዛኞቹን ይዞ ለሕግ አስረክቧል፡፡ የተፈጸመበትን ክህደት በበቀል ሒሳብ ሳይሆን የሕግ ማስከበር መርሕን በተከተለ መንገድ ሲያከናውን ነበር፡፡ በጦርነት ውስጥ ለመርሕ መገዛት ቀላል አይደለም፡፡ ሠራዊታችን ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከሽብር ቡድኑ ጋር አያሌ ውጊያዎችን ሲያደርግ ብዙ ዋጋ ከፍሏል፡፡ በየጦር ውሎው በጀግንነት እየተዋጋ ለእናት ሀገሩ ተሠውቷል፡፡ ለሀገርና ለወገን ያለውን አጋርነት በንግግር ሳይሆን በተግባር አሳይቷል፡፡ አሁንም በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ነው፡፡

ዛሬ ሽብር ቡድኑ የተሰጠውን የጥሞና ጊዜ እንድ እድል ከመጠቀም ይልቅ እንደ ድል ወሰደው። በአማራና በአፋር ክልል በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የግፍ በትሩን ቀጥሎበታል፡፡ የጥፋት አጋሩ ሸኔም በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ ልዩ ልዩ አደጋዎችን እየጣለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን ረፍት እየነሣ ነው፡፡ ሌሎችም የጥፋት ኃይሎች ከውስጥም ከውጭም ወኪሎቻቸውን አስተባብረው በሙሉ ዐቅማቸው ኢትዮጵያ ላይ መዝመታቸውን ገፍተውበታል፡፡

ሠራዊታችን ብቻውን ተጋፍጦ የድል ዜና እንዲያበስረን መጠበቅም ሞኝነት ነው፡፡ ጠላቶቻችን ተባብረው የደቀኑብን አደጋ ሁላችንም ተባብረን ካልመከትነው ድል የማይታሰብ ነው፡፡ የጠላቶቻችን ኅብረት ለፕሮፓጋንዳ የተፈበረከ ጉዳይ አይደለም፡፡ እውነት ነው፡፡ እነዚህ ኃይሎች ዓላማቸው ግልጽ ነው፡፡ ብረት ያነሡት ሀገር ለማፍረስ እንጂ ሀገር ለመገንባት አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን ስም በክፉ የሚያብጠለጥሉ፣ ነገ የሊቢያና የሶርያን እጣ ሊያስታቅፉን እንዲመቻቸው የፈጠሩት ዘዴ መሆኑን ልናውቅ ይገባል፡፡ ጠላቶቻችን በዚህ ደረጃ ሲተባበሩብን እኛ አንድ የማንሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ የወንድምና የእኅቶቹ ጥቃት የሚያንገበግበው ሁሉ ጣት ከመጠቆም ወጥቶ ሀገር የማዳን ፍላጎቱን በተግባር መግለጥ አለበት፡፡

ወደፊት ታሪክ ፍርዱን ይሰጣል፡፡ ፈሪውም በፈሪነቱ፣ ሴረኛውም በሴረኛነቱ እንደየግብሩ ይመዘገባል፡፡ የሽብር ቡድኑን ትውልድ በክህደት ሲያስታውሳቸው እንደሚኖር ግልጽ ነው፡፡ በተቃራኒው በግፍ የተሠውት የሰሜን ዕዝ አባላትን ጨምሮ ለሀገር የሚዋደቁ ጀግኖች ስማቸው በወርቅ ይጻፋል፡፡

ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ ለተሠዉ ጀግኖቻችን!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጥቅምት 24፣ 2014 ዓ.ም
ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ ለተሠዉ ጀግኖቻችን!

Kabajni gootota keenya Itoophiyaaf jedhanii aarsaa ta'aniif!
Best Bluetooth Speaker Sound Quality