Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
114K subscribers
5.1K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
500 ሚልዮን ችግኞች በአንድ ጀንበር
በግብጽ ካይሮ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታሕ ኤልሲሲ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትብብር በሰፈነበት መንፈስ ውይይቶች አካሂደናል።

Pleased to have met with President Abdelfattah Elsisi in Cairo, Egypt for talks marked by the spirit of cooperation on bilateral and regional issues of mutual interest.
‏أثيوبيا تحفظ الأمانة، ولا تنوي الإضرار بدول حو؜ النيل الشقيقة
ዓላማችን ሪከርዳችንን መስበር ነው!

የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዳይ ኢትዮጵያን የመጠበቅ፣ የማክበርና የማበልጸግ ጉዳይ ነው። ታሪክ የመቀየር ጉዳይ ነው። ለትውልድ የመትረፍ ጉዳይ ነው።

ከማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ ተግባራት ነጻ የሆነ ቀን የመረጥነው ይህ ቀን ሊያልፈው የሚገባ ኢትዮጵያዊ ስለሌለ ነው። ሰኞን ስንመርጥ የሥራ መጀመሪያችንን ተፈጥሮን በመታደግ እንድንጀምር ነው።
ፉክክራችን ከራሳችን ጋር ነው። ክልሎች፣ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና መንደሮች ከአምናው የበለጠ በመትከል የየራሳቸውን ሪከርድ እንደሚሰብሩ እናምናለን። እያንዳንዳችንም የየራሳችንን ሪከርድ መስበር አለብን።

ችግር የራሱን ሪከርድ እንዲሰብር ልንፈቅድለት አይገባም። ችግር የራሱን ሪከርድ ከሰበረ ተሸንፈናል ማለት ነው። ችግርን የምናሸንፈው መጀመሪያ የራሳችንን ፣ ቀጥሎ የአካባቢያችንን፤ በመጨረሻም የዓለምን ሪከርድ ስንሰብር ነው።

እኔ ነገ በተደጋጋሚ ለመትከል ተዘጋጅቻለሁ። እናንተስ?
ነገ ሐምሌ 10 ቀን 2015 የራሳችሁን ሪከርድ በብዙ መጠን እስክትሰባብሩ ድረስ ዛፎችን ለመትከል ተዘጋጁ።
እኛ ጀምረናል! እናንተስ? Nuti jalqabneerra! Isinoo?
የምንተክለው ለቀጣዩ ትውልድ ነው::
Kan dhaabnu dhaloota dhufuufidha.
We are planting for the next generation!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ለኢትዮጵያም፣ለአፍሪካም እና ለአለም እጅግ የሚያኮራ ተግባር ፈጽመናል።
ታሪክ ሠርታችኋል

500 ሚልዮን ዛፎችን በመትከል የራሳችንን ሪከርድ እንድንሰብር የቀረበውን ጥሪ ተቀብላችሁ የወጣችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል። አረንጓዴ ታሪክ ሠርታችኋል። አረንጓዴ ታሪክ ጽፋችኋል።

የተዛባ አየር፣ የተራቆተ ምድር ለትውልድ አናወርስም ብላችሁ፤ ጎሕ ሳይቀድ ወደ ተራሮችና ሸለቆዎች፣ ወደ ሜዳዎችና ሸንተረሮች ተሠማርታችሁ 566 ሚልዮን ዛፎች ተክላችኋል። ሪከርዳችሁን ሰብራችኋል።

በሁሉም ክልሎች፣ ዞኖችና ወረዳዎች ዛፎች ተተክለዋል። ከ9 ሺ በላይ የተለዩ ቦታዎች ተዘጋጅተው ነበር። ከ3600 በላይ የሚዲያ ባለሞያዎች በመላ ሀገሪቱ ተሠማርተው ነበር። የቴሌና የግብርና ባለሞያዎች የመረጃ አያያዙ ዘመናዊ እንዲሆን ሠርተዋል። የአዲስ አበባ ታክሲዎች ነጻ ትራንስፖርት ለችግኝ ተካዮች ተሰጥተዋል። ሕጻናት፣ እናቶች፣ አባቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ በነቂስ ወጥተው ተክለዋል። በኢትዮጵያውያን አረንጓዴ ታሪክ ተሠርቷል።

ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የማንሰብረው ሪከርድ የለም።
The Benefits of Using a YT Audio to MP3 Converter