Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
112K subscribers
5.01K photos
248 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ከተጠጉ የሶሪያ ስደተኛ ወንድምና እኅቶቼ ጋር የረመዳን ኢፍጣር ማዕድን ተጋርተናል። ይህ አጋጣሚ ገና በኢስላም ማለዳ ቀናት አያቶቻችን የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የቅርብ ዘመዶችና ሶሃቦችን ተቀብለው ያስተናገዱበትን አንፀባራቂ ታሪክ የሚያስታውሰን ነው።

በዚህ ድንቅና ውብ ታሪካችን እንደምኮራው ሁሉ፤ ሕዝባችን በተለይም በወጣቱ ትውልድ ውስጥ ለተቸገሩ፣ ለተሰደዱና ጎዳና ላይ ለወደቁ የሰብአዊነትና የእምነት ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ትኩረት እንዲሰጡ እንሻለን። ይህ ሁኔታ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዛሬም ወደፊትም ከሙስሊም ሀገራትና ሕዝቦች ጋር በወዳጅነት፣ በፍቅርና በሰላም ለመኖር ያለንን ጠንካራ ፍላጎትና እምነት የሚያጸና ነው።

‎لقد شاركنا اليوم بماءدة الإفطار الرمضانية إخواننا وأخواتنا من اللاجئين السوريين المتواجدين في أثيوبيا. ويعيد هذا الحدث الي أذهاننا وذاكرتنا الجماعية نحن الأحباش كيف إستقبل أجدادنا وأمجادنا المهاجرين من الصحابة الأجلاء وأقرباء النبي سيدنا محمد (صلعم) في فجر الإسلام.

‎وكما نفتخر ونعتز بذالك التاريخ الجلي نكرس لذى شعبنا وخاصة جيل الشباب ثقافة الإهتمام بالمهاجررين، والمسكين وأبناء السبيل من إخواننا وأخواتنا في الإيمان والإنسانية. وتصب كل هذه الظواهر في الحاضر والماضي في رغبتنا المخلصة والصادقة بأن نعيش مع أخواننا من الشعوب الإسلامية بالوئام والمحبة والسلام دائما وأبدا.
በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲወለድ የዜጎች ንቁ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ ነው። በተለይ በምርጫ ወቅት ዜጎች በልዩ ልዩ መንገዶች ተሳትፎአቸውን ሊያረጋግጡ ይችላሉ። ካርድ ወስደው በሰላማዊ መንገድ ለመምረጥ ራስን ከማዘጋጀት በዘለለ፣ በሲቪክ ማኅበራት አማካኝነት የምርጫው ሂደት ግልጽና ተአማኒ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ይጠበቃል፤ ለምሳሌ፡- በካርድ አሰጣጡ ዙሪያ፣ የምርጫ ቅስቀሳን በተመለከተ እና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ ቁጥጥር ያደርጋሉ። በተጨማሪም ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን በቅድመና ድህረ ምርጫ ወቅት የሚያጋጥሙ ግጭቶችን ለማስቀረት ዜጎች የማይተካ ሚና እንዳላቸው መዘንጋት የለበትም።
የብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ መግለጫ
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ።

Hordoftoota Amantaa Kiristaanaa maraaf Ayyaana gaarii isiniif haa ta'u !

Baga geessan !
The Best Dell Monitor for Your Needs