Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
114K subscribers
5.11K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
እንኳን ለግንቦት ሃያ የድል መታሰቢያ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።

ግንቦት ሃያ የዘመናዊት ኢትዮጵያን ታሪክ ከቀየሩ ዕለታት መካከል አንዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ለማድረግ አያሌ ታጋዮች እጅግ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ነፍስ ሠውተዋል፡፡ የግንቦት ሃያ ታጋዮች የነፍስ ዋጋ የከፈሉለት ዓላማ ግፍና ጭቆና፣ አድሎና ወገንተኝነት ቆሞ፤ እኩልነት ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ነው፡፡

ግንቦት ሃያን ማክበር ያለብን እነዚህን ዓላማዎች እያሰብን መሆን አለበት፡፡ ቀኑን የምናስበው በግንቦት ሃያ ላይ ተቸክለን ሳይሆን ወደፊት እየሄድን የኋላውን እየገመገምን መሆን አለበት፡፡ ግንቦት ሃያን ያመጡ ታጋዮች ዓላማ ኢትዮጵያን ወደ ግንቦት ሃያ ሁለት መውሰድ እንጂ ወደ ግንቦት አሥራ ዘጠኝ መመለስ አልነበረም፡፡ ሀገራቸው በሁሉም መመዘኛ ግንቦት ሃያን አልፋ፣ ግንቦት ሃያ አንድንም ተሻግራ፣ ወደ ግንቦት 22 መድረስ ነበር፡፡

የግንቦት ሃያ ታጋዮችን ዓላማ የምናሳካው በሁለመናዋ ከግንቦት 19 የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት ከቻልን ብቻ ነው፡፡ የብልጽግና ጎዳናችን ዓላማ ግንቦት ሃያ ላይ ቆሞ ግንቦት አሥራ ዘጠኝን እያሰቡ መኩራራት ሳይሆን ሀገራችን ወደ ግንቦት 22 ማስፈንጠር ነው፡፡ ይህ ማለትም ሀገራችን ከነበረችበት አስከፊ ሁኔታ ማላቀቅ ብቻ ሳይሆን መድረስ ወደነበረባት የላቀ ደረጃ ማድረስ ነው፡፡ የግንቦት ሃያ የድል መታሰቢያ በዓልን ሰናከብር በተባበረ ክንድ ከግንቦት ሃያ የሚልቅ፣ ወደ ግንቦት 19 እንዳንመለስ የሚያደረግ ምጡቅ ሥርዓት ለመገንባት ቃላችን የምናድስበት እና ወደ ላቅ ውጤት ለመቀየር ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የምንገባበት መሆን ይገባዋል፡፡
ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ በአጥንትና ደማቸው ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ላቆዩ ሰማዕታት!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ

ግንቦት 19/ 2012 ዓ.ም

//
* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *
* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *
ኢትዮጵያ ወደ ውጪ በመላክ የውጪ ምንዛሬ ከምታገኝባቸው ዋነኛ ምርቶች መካከል የዘይት እህሎች ይገኙበታል፡፡ የዘይት እህሎችን በማምረት እና በማሠራጨት ሂደቱም፣ ከ3 ሚሊየን የሚበልጡ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ይሳተፉበታል፡፡
እንዲያም ሆኖ፣ ኢትዮጵያ የምግብ ዘይትን በከፍተኛ መጠን ከውጪ ከሚያስገቡ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡ ከ95 በመቶ የሚበልጠው የሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚሸፈነው ከውጪ ሀገራት በሚገባ ዘይት አማካኝነት ነው፡፡ በየዓመቱ ዘይትን ከውጪ ሀገራት ለማስገባት የሚወጣው አማካይ የገንዘብ መጠን ከ400 ሚሊየን ዶላር ይበልጣል፡፡

ጎጃም በሚገኙት የቡሬ ዳሞት እና የደብረ ማርቆስ አካባቢዎች የግሉ ዘርፍ የምግብ ዘይትን በአግሮ አንደስትሪ ኩታ ገጠም እርሻዎች አማካኝነት የማምረቱን ሥራ በመጀመር ላይ ይገኛል፡፡
ሥራው ቀጣይ የምርት ሂደቶች እንዲሳኩ ለማድረግ የሚያስችል ሲሆን፣ ምርቱ ደግሞ ለኩታ ገጠም አምራቾቹ ትርፋማነትን ያስገኛል፡፡ በዶሮ እርባታ፣ በወተት እና የወተት ተዋጽዖ ምርቶች እንዲሁም ከብት በማደለብ ተጨማሪ ሥራዎችን ለመፍጠርም ያስችላል፡፡ በዚህ መልኩ፣ የሀገር ውስጥ ፍጆታን መሸፈን እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

Hoomishawwan Itoophiyaan biyya alaatti erguudhaan sharafa alaa ittiin argattu keessaa min'aanonni zayitaa kan argamanidha. Adeemsa min'aanota zayitaa hoomishuufi raabsuu keessattis qonnaan bultoota qabiyyee xiqqaa qaban miliyoonna sadii olitu hirmaata......

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
ኮሮና ከሚያሸንፈን እናሸንፈው። ከሚዘምትብን እንዝመትበት። ከሚያጠፋን እናጥፋው።

የኮሮና ወዳጅ ማን እንደሆነ ደርሰንበታል። መዘናጋት ይባላል። ኮሮና ከመዘናጋት ጋር ከተባበረ አንችለውም። ሁለቱን መነጣጠል አለብን።

ሰሞኑን በኮሮና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ለምን? ኮሮናና መዘናጋት ግንባር ፈጥረዋል ማለት ነው።

ኮሮና ማንን እንደሚጠላና እንደሚፈራ ዐውቀነዋል። ኮሮና ጥንቃቄ የሚባለውን ፈጽሞ አይወደውም።
ጥንቃቄ ባለበት ወይ አይደርስም ፤ ወይ የከፋ ጉዳት አያደርስም።

እንደምታዩት ሁለት፣ ሦስት፣ ዐሥር፣ ሠላሳ፣ ሰባ፣ እያለ መቶ ገብቷል።
ሁኔታው የሚያሳየው ኮሮና እያመረረ፣ እኛ እየተዘናጋን መምጣታችንን ነው።

ኮሮና ተዘናግቶ እኛ ብናመር ነበር ጥሩ።
ወይ ተባብረን እንነሣበት፤ አለያም ኮሮናና መዘናጋት ተባብረው ይደቁሱን?
ምርጫው ከሁለቱ አንዱ ነው?

ሁኔታው ሳይመርብን፣ እኛ እናምርበት። ኮሮና ሳያሸንፈን እናሸንፈው። ኮሮናን የማሸነፊያ ቀን ዛሬ፣ የማሸነፊያ ሰዓት አሁን፣ የሚያሸንፈውም ሰው እርስዎ ነዎት።

//
* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *

* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *
ከዓለም የምግብ ፕሮግራ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዴቪድ ቤዝሊ ጋር ኢትዮጵያ የሰብአዊ ርዳታዎችን በማስተባበር ስለምትጫወተው ሚና፣ ስለዚህ ዓመት #አረንጓዴ ሻራ ዕቅዶች ድጋፍ እና ኢትዮጵያ የምግብ ደኅንነትን ለማረጋገጥና ምርታማነትን ለማሳደግ ስለምታደርገው ጥረት ጥሩ ውይይት አድርገናል፡፡

Hoji Raawwachiisaa Olaanaa Sagantaa Nyaata Addunyaa Deevid Beeziley waliin gahee Itoophiyaan gargaarsota namoomaa qindeessuudhaan qabdu, waa'ee deeggarsa karoora #AshaaraaMagariisaa baranaafi tattaaffii Itoophiyaan wabii nyaataa mirkaneessuufi hoomishtummaa guddisuuf gootu irratti marii gaarii gooneerra.

// * በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *

* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *
የለውጥ ጉዞ ረጅምና በውጥንቅጦች የተሞላ ነው፡፡ የለውጥ ዐውዳችን የተለያዩና ብዙ የሆኑ ፍላጎቶች የሚስተናገዱበት ውስብስብ መድረክ ነው ፡፡ አዎንታዊ ለውጥ ትግልን ከትዕግሥት ጋር ሳያዛምዱ አይመጣም። የሚታገሉ ይለውጣሉ፤ የሚታገሡ የለውጡን ውጤት ያያሉ:: ለብሔራዊ አንድነትና አብሮነት ሲባል በየቀኑ በትጋትና በትዕግሥት መሥራት ይጠይቃል ፡፡ ለ#ኢትዮጵያ ብልጽግና የማይረዱ አጀንዳዎች እንኳን ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበታችንን፣ ጆሯችንንም ሊያገኙ አይገባም፡፡

Adeemsi jijjiiramaa dheeraafi bu'aa bayiidhaan kan guutamedha. Haalli qabatamaa jijjiirama keenyaa nuti keessatti hojjennu waltajjii walxaxaafi fedhiiwwan adda addaa hedduun keessattia kan keessumsiifamanidha. Jijjiiramni gaariin qabsoo obsa waliin godhamu malee hindhufu. Warri qabsa'an ni jijjiiru; warri obsan immoo bu'aa jijjiiramichaa ni argu. Tokkummaa biyyaalessaafi waliin jireenyaaf jecha guyya guyyaatti ciminaafi obsaan hojechuu gaafata. Ajandaawwan #badhaadhina Itoophiyaatiif hin gumaachine yeroo, maallaqaafi humna keenya miti, gurra keenya argachuu hin qabani.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ አበባን እንደ ስሟ የምታፈራ አበባ እናደርጋታለን::
ዓርብ ግንቦት 28፣ 2012 ዓመታዊውን የ#አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ በይፋ እንጀምራለን። ባለፈው ዓመት እያንዳንዳችን ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለን፣ ያቀድነውን አሳክተናል። ከ#ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር እየተፋለምን ቢሆን፣ 5 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ዕቅዳችንን እናሳካዋለን። እያንዳንዱ ቤተሰብ አካላዊ ርቀትን እንደ ጠበቀ ዐሻራውን ማሳረፍ የሚችልበትን መንገድ እናመቻች።

Jimaata, Caamsaa 28/2012 dhaabbii biqiltuu waggaa #AshaaraaMagariisa ifatti jalqabna. Bara darbe tokkoon tokkoo keenya waamicha biyyaalessaa kana fudhannee kan karoorfanne fiixaan baafneerra. Weerara #COVID-19 waliin wal'aansoo walqabaas ta'u, karoora keenya biqiltuuwwan biliyoona 5 dhaabuu galmaan ni geenya. Maatiin mata mataatti gargar fageenya qaamaa eegaa haala itti ashaaraa isaa kaa'uu danda'u ni mijeessina.

* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *

* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *
ባላሰበው መንገድ ባልጠበቀው ዘዴ
ኮቪድን መመከት ይቻል ኖሯል እንዴ።
በአየር ላይ ሆነና የኮቪድ ነገሩ
አፍና አፍንጫችን ተያዙ ታሠሩ፤
አየር የሚበክል ቫይረሱ ሲመጣ
እኛም እንተክላለን ተፈጥሮን አቃንቶ አየር የሚያነጣ።
አዙሪቱን ሰብሮ ከኮሮና ወዲያም ታሪክ የሚሠራ
እናሳርፋለን አረንጓዴ ዐሻራ።

Karaa hin yaadamneen mala hin eegamneen
COVID19 ittisuun nin danda'ama turee

waa'een koronaa qilleensarra ta'eeti
Afaanii fi funyaan keenna qabamanii hidhamanii

Vaayrasiin qilleensa faalu yennaa dhufu
Nutis nin dhaabna uumama bareechee kan qilleensa qululleessu

Jaanjummaa cabsee Koronaan alattis seenaa kan hojjatu
Nin keenna ashaaraa magariisummaa

//
* በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ *
* Qaamaan gargar fagaannee, qulqullina eegnee, waliikeenya walgargaarree, Itoophiyaa Koroonaa irraa haa baraarru! *
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ

ላለፉት ጥቂት ወራት ዓለም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ፈተና ውስጥ ገብታ ቆይታለች። የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር ሁላችንም ኃላፊነታችንን በመወጣት ላይ እንገኛለን።

ይህ ጊዜ እንድናውቅ ያደረገን አንድ ነገር ቢኖር የሰውን ልጅ ተጋላጭነት፣ የግል ጤንነትን የመጠበቅ አስፈላጊነትና ጤናማ አካባቢን የመፍጠር አስፈላጊነት ነው ። ብዝኃ ሕይወትን መጠበቅና መከባከብ ቅንጦት ሳይሆን ህልውናመሆኑን አይተናል።
ልክ እንደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች ኢትዮጵያም የአየር ሁኔታ ለውጥና የአካባቢ መራቆት ችግር ተጋርጦባታል። እንዲህ ዓይነት ችግሮች ለጎርፍ አደጋ ፣ ለአፈር መሸርሸር ፣ ለደን መጥፋትና ለብዝኃ ሕይወት ኪሳራ ዳርገዋታል።

የአየር ሁኔታ ለውጥን መመከትና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕድገት ሁኔታዎችን ማመቻቸት የብልጽግና ጉዟችን አንዱ ጎማ ነው ። በዓለም አቀፍ ደረጃ የዓለም የአካባቢ ቀንን ስናከብር ፣ በኢትዮጵያ የ2012 የአረንጓዴ ዐሻራ ብሔራዊ መርሐ ግብራችንን በይፋ ጀምረናል። ከፊታችን እየመጣ ባለው የክረምት ወቅት 5 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታጥቀንና ቆርጠን ተነሥተናል።

ይህ ግብ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ 20 ቢሊዮን ዛፎችን ለመትከል የያዝነው ራእይ አካል ነው። ባለፈው ዓመት በጀመርነው የአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ፣ በ20 ሚልዮን ወገኖች እጅ 4 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል ። በአንድ ቀን ብቻ ወደ 354 ሚሊዮን የሚጠጉ ችግኞችን በመትከል ታሪክ ቀይረናል። ከተከልናቸው መካከልም በአጠቃላይ 84 በመቶ ጸድቀዋል።

ባለፉት ወራት ለዚህ ዓመት የተከላ ወቅት ሀገር አቀፍ ዝግጅቶች ሲደረጉ ቆይተዋል ......

https://www.facebook.com/PMAbiyAhmedAli/
How to Make a Poster on Word