Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
114K subscribers
5.11K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
የሀገር ግንባታ የጋራ ጥረት ነው። እያንዳንዳችን ለኢትዮጵያ ስኬት ሚና አለን። በተቀናጀ ጥረታችን እንቀጥል።

Ijaarsi biyyaa tattaaffii walooti. Tokkoon tokkoon keenya milkaa'ina Itoophiyaatiif gahee qabna. Tattaaffii keenya qindaawaadhaan itti haa fufnu.

Nation building is a collective effort. Each one of us plays a critical role in #Ethiopia’s success. Let’s continue building on these efforts.
ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፣ በሩቅ እና ቅርብ ያሉ፣ የሀገራችንን በጎ የማይፈልጉ አካላት ያለ የሌለ ሀብትና ጉልበታቸውን ተጠቅመው፣ በሀገራችን ላይ የተበላሸ ትርክትን የመጫን ጦርነት ውስጥ መክፈታቸውን አንዘንጋ። በብሔር ላይ እየተሠራ ያለውን የተዛባ ትርክት ለመቀልበስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን ሚና መጫወት አለበት። በኅብረ ብሔራዊ አንድነት የራሳችንን ታሪክ እኛው እንሠራለን፤ እኛው እንጽፋለን!

My fellow Ethiopians, let us not forget that we are also engaged in a sophisticated narrative war waged against the nation with many using disinformation as a pathway for their sinister moves. Each Ethiopian must play a role in pushing back and reversing the distorted narrative. In unity we can write our own story.
ጽናት!
Cimina!
Resilience.

#Ethiopia
ሀገሪቱ ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ሥጋቶችን ስትጋፈጥ ብዙ ትግሎች እና ምቾት ማጣት ይኖርብናል። ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እንድናቋርጠው እጠይቃለሁ። በአንድነት ከቆምን ማሸነፋችን ሰበር ዜና አይሆንም! ከዚህ በፊት አድርገነዋልና። አሁንም እናደርገዋለን።

Wayita biyyi yaaddoo keessaafi alaatiin wal'aansoo walqabdu kana bu'aabayiifi waan mijaawaa hin taane hedduun ni jiraata. Itoophiyaanotni hundi keenya tokkummaadhaan dhaabannee bubbee yeroof mul'atu kana keessa kunnee akka darbinun isin gaafadha. Tokkummaadhaan dhaabannaan injifachuun keenya oduu haaraa nutti hin ta'u. Kanaan dura waan goonee argineef. Ammas kana ni goona.

While there are many struggles and discomforts we may have to face as the nation confronts both external and internal threats, I ask all Ethiopians to stand in unity and ride this passing momentary wave. Standing together we CAN overcome! We have done it before. And we will do it now.
በኢትዮጵያ እና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፣ እውነትን ለዓለም ለመግለጥ እያደረጋችሁ ያላችሁት ተጋድሎ እጅግ የሚደነቅ ነው። ይህ ጥንታዊ ሕዝብ ከሩቅ እና ከቅርብ ኃይሎች የተጋረጠበትን የህልውና ስጋት አንድ ሆነን ማሸነፍ እንችላለን። እንደ #አድዋ ልጆች #ኢትዮጵያን #በጽናት ወደፊት እናሻግራለን።

Itoophiyaanonni lammiikoo biyya keessaafi alatti argamtan qabsoon dhugaa jiru addunyaatti mul'suuf gootan kan baay'ee dinqisiifatumudha. Yaaddoo jiraachuu humnoota dhihoofi fagoorraa biyya dursituu kanarratti danqarame tokko taanee moo'achuu ni dandeenya. Akka ijoollee #Aduwaa #Itoophiyaa jabinaan fuulduratti ni ceesifna.

My fellow Ethiopians here and in the Diaspora, your role in telling the world the truth is commendable. In unity, we can overcome the existential threat this ancient nation is confronted with by forces far & near. As children of #Adwa, we will carry #Ethiopia #ResilientlyOnwards.
መደመር የመከፋፈል አጥሮችን ደርምሶ ወደ አንድነት መምጣት ነው። ባለፉት 3 ዓመታት ባደረግናቸው የቀጣናዊ ውሕደት ጥረቶች የሕዝብ ለሕዝብ ትሥሥር ወሳኝ ነበር። ተደምረው ለእውነት ለቆሙ ኢትዮጵያውያን እና የአፍሪካ ቀንድ ዳያስፖራዎች አድናቆቴን እገልጻለሁ። #በቃ

Medemer is about coming together beyond lines of division. In the regional integration efforts we have been undertaking the past 3 years, the people to people ties have been critical. My appreciation to Ethiopians & Horn Region Diaspora who are emulating Medemer by coming together. #NoMore
“ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን!

ውድ የሀገሬ ልጆች፣
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጀግንነትና መሥዋዕትነት ክብሯንና ነጻነቷን አስጠብቃ የኖረች ሀገር ናት። ይሄን ወዳጅም ጠላትም ያውቀዋል። ድንበሯን ሊደፍሩ የሞከሩ አይበገሬ ክንዷን አይተዋል። ሊያስገብሯት የቋመጡ አቀርቅረው ተመልሰዋል። ክህደት ለፈጸሙባት ተገቢውን ትምህርት መስጠት፣ ከጀርባ የወጓትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣትን ታውቃለች። ለሺህ ዘመናት የተጎናጸፈችው ነጻነትና ሉዓላዊ ክብር በችሮታ የተገኘ አይደለም። ያለ ዋጋ ነጻነትን አጽንቶ መጠበቅ አይቻልምና፤ ኢትዮጵያ የሚለው የነጻነት ስም የደም ዋጋ ተከፍሎበታል፣ ብርቱ ጀግኖች ሞተውለታል።

በታሪክ የምናውቃቸው አባቶቻቸው በአስተዳደርና በርእዮተ ዓለም ይለያያሉ፤ ለመብት፣ ለፍትሕና ለእኩልነት በነበራቸው አመለካከት ይለያያሉ። ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነት፣ ነጻነትና ሉዓላዊነት ባላቸው ቦታ ግን ልዩነት አልነበራቸውም። በቋንቋ፣ በብሔርና በጎሳ ብዝኃነት ቢኖራቸውም የአልደፈርም-ባይ ቆራጥነታቸው አንድ ያደርጋቸዋል። የግል ፍላጎታቸው የቱንም ያህል የተራራቀ ቢሆን፣ የጋራ ጠላት ሲመጣ ኢትዮጵያዊነት ከግላዊነታቸው በላይ ይቀመጣል።

ድሮም ሆነ ዛሬ የእያንዳንዳችን ፍላጎት፣ የሁላችንም ሕይወት ከኢትዮጵያ በታች ነው። እኛ ኖረን ኢትዮጵያ ከምትሞት እኛ ሞተን ኢትዮጵያ እንድትኖር እንፈልጋለን። የሁላችንም የሆነች፣ ነጻነትና ፍትሕ የሰፈነባት፣ በገናናነቷና በነጻነቷ በዓለም አደባባይ የምትጠራ ሀገር እንድትኖረን ምኞታችን ነው። ለኢትዮጵያ ትልቅ በመመኘት፤ ሀገራችን አንገቷ ቀና እንዲል በመፈለግ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ዐቅማችን የፈቀደውን ሁሉ አድርገናል። ፖለቲካችን ከመገዳደል ወደ መተጋገል እንዲቀየር ታግለናል። ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በሰው ሀገር የሚንከራተቱት ሁሉ እንዲገቡ ለማድረግ ሞክረናል። ካለፈው በጎውን ወስደን ጥፋቱን በይቅርታ ለማረም ተንቀሳቅሰናል። “በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር” ብለን አዲስ ምዕራፍ ከፍተናል። የመለያየትና የጥላቻን ግንብ አፍርሰን የመደመርና ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ድልድይን ልንገነባ ቃል የገባነውን ወደ ተግባር ለመተርጎም ዐቅማችን የፈቀደውን አድርገናል።

ኢኮኖሚው እንዲያገግምና መዋቅራዊ ለውጥ እንዲያመጣ፤ የዳኝነት ሥርዓታችን እንዲሻሻል፣ የሰብአዊ መብት አያያዛችን እንዲስተካከል፤ የውጭ ግንኙነት መርሐችን ጎረቤት ተኮር እንዲሆን ታግለናል። በዚህ መካከል እንደ ሰው በርትተናል። እንደ ሰውም ደክመናል። እንደሰው አልምተናል፣ እንደ ሰውም አጥፍተናል። በኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ በኢትዮጵያ ክብርና በኢትዮጵያ ታላቅነት ግን ለአፍታም አዘንብለን አናውቅም።

ኢትዮጵያ የምታጓጓ ሀገር ናት። ከትናንትናዋ ይልቅ ነገዋ ታላቅ ነው። መከራ ማለፍ ነባር ችሎታዋ ነው። ይሄንን የገጠመንን መከራም እናልፈዋለን። ኢትዮጵያ ማሸነፏ አይቀርም። አሁን ኢትዮጵያን ለመታደግ የመጨረሻውን ፍልሚያ የምናደርግበት ጊዜ ላይ ነን። ጠላቶቻችን በውጭና በውስጥ ተቀናጅተው ዘምተውብናል። በአንድ በኩል ታሪካዊ ጠላቶቻችን በራሷ ፈቃድና በራሷ መንገድ ብቻ የምታድግ ኢትዮጵያ ላለማየት የጥፋት በትር ሰንዝረዋል። ኢትዮጵያ አፍሪካዊ በሆነ መንገድ ከተነሣች፣ ተነሥታም ካሸነፈች፣ ከዚህ በኋላ ለማንም የማትመለስ ትሆናለች። ይሄን አፍሪካዊ መንገድ ለማደናቀፍ ሁሉንም ዓይነት የክፋት መሣሪያዎች አሰልፈዋል። የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን የእነርሱን ብርታት በኢትዮጵያ ድካም ላይ ለመገንባት ተነሥተዋል። የኢትዮጵያ ፍላጎት ይዞ ማለፍ እንጂ ጥሎ ማለፍ አልነበረም፤ ለዚህ ነው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን በዋናነት ጎረቤት ተኮር እንዲሆን ያደረግነው፤ ይህ ትግል የመላ ጥቁር ሕዝቦች ትግል ነው። ኢትዮጵያ አንበርክኮ ጥቁር ሕዝብን ለማሳፈርና አዲሱን የቅኝ ግዛት ቀንበር ለመጫን የሚደረግ ሤራ ነው።
ጥቁር ሕዝቦች የራሳችን ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ክብር እንዳይኖረን ሆን ተብሎ የሚደረግ አንገት የማስደፋት ትግል ነው። ይህ በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተ ዘመቻ፣ ኢትዮጵያን በማንበርከክ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነትና የአሸናፊነት አርአያ እንዳያገኙ የተከፈተ ዘመቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። ለጥቁር ሕዝብ ክብርና ልዕልና ስትሉ፣ በፓን አፍሪካ መንፈስ፣ ሁላችሁም ጥቁር ሕዝቦች፣ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቆሙ ጥሪ አቀርብላችኋለሁ።

በመጨረሻም ይህ ትግል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ነው። ልጆቻችን ሀገር እንዲኖራቸው የሚደረግ ትግል ነው። ልጆቻችን ክብርና ነጻነትን ለብሰው፣ በዓለም አደባባይ በኩራት ቀና ብለው እንዲሄዱ የሚደረግ ትግል ነው። በዓለም ላይ በክብር የምንጠራበት ስም እንዲኖረን የሚደረግ ትግል ነው። መኖር ወይም አለመኖራችንን የሚወስን ትግል ነው። ያለ ጥርጥር ግን እናሸንፋለን። ኢትዮጵያን ጠርቶ መሸነፍ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው።

ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ፡፡ የእኛ መዝመት የሚፈጥረውን ክፍተት ከግንባር የቀሩት በሙሉ ዐቅማቸው ሸፍነው ይሠራሉ፡፡ በግንባር ያልተሰለፉ የክልልና የፌደራል አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ የልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሙሉ ዐቅማቸው ይከውናሉ።

ጎልማሶች በዘዴና በብልሃት አካባቢያቸውን እየጠበቁ፣ አረጋውያን እናትና አባቶች በጸሎት እየተጉ፣ ሁሉም ሰው ተባብሮ የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያረጋግጣል። ከዚህ በኋላ በሩቁ ተቀምጠን ተቺና አራሚ የምንሆንበት ጊዜ አይደለም። መደረግ ያለበትን እኛው ራሳችን እናድርገው። ለኢትዮጵያ ከእኛ በላይ ከየትም አይመጣም። ኢትዮጵያ የሚለው ስም የአሸናፊዎች ስም ነው፤ የነጻነት ምልክት ነው። አልጠራጠርም፣ የእኔ ትውልድ ለአሸናፊ ስሙና ለነጻነት ምልክቱ የሚጠበቅበትን ዋጋ ከፍሎ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በክብር መዝገብ ላይ በወርቅ ብዕር ያትማል።

አመሰግናለሁ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትሩር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ኅዳር 13፣ 2014 ዓ.ም
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች አሥራ አንደኛ ክልል ሆኖ ፌዴሬሽኑን ተቀላቅሏል። የጀመርነው የለውጥ ጉዞ ፖለቲካዊ መብቶችን በመጠቀም ረገድ ያስገኘውን ውጤት አንዱ ማሳያ ነው። ኅብረ ብሔራዊነት አንድነትን የማጽኛ ዕሴት ነው። ፌዴራላዊ ሥርዓት ሕዝብ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ሀገር የሚገነባበት ሥርዓት ነው። ይሄንን በተግባር አሳይተናል። ሰላማዊ፣ ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ሕገ መንግሥታዊ መብታችሁን ተጠቅማችሁ፣ አሥራ አንደኛውን ክልል ለመሠረታችሁ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ።

The People of Southwestern Ethiopia have joined the federation as the eleventh region. This is a testament to the journey of reform we have taken in the exercise of political rights. Diversity is one of the pillars of unity. A federal system is a system in which the people govern themselves and build their country. We have demonstrated this in practice. Congratulations to the people of Southwest Ethiopia for exercising your constitutional rights in a peaceful, legal and democratic manner to establish the 11th region.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምንፈልገው ወይ ኢትዮጵያዊ መሆን ወይም ኢትዮጵያ መሆን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በሁሉም መስክ ተባብሮ ሲነሣ ውጤቱ ድል ነው። በግንባር፣ በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በኮሙኒኬሽን፣ በስንቅ ዝግጅት፣ ዘማች በመከባከብ፣ ጸጥታ በማስከበር፣ተፈናቃዮችን በመደገፍ. በሁሉም ግንባሮች ለዘመታችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

Uummanni Itoophiyaa gama hundaan tumsee yoo ka'e bu'aansaa injifannoodha. Warri gama addawwan waraanaatiin, dippiloomaasiidhaan, dinagdeedhaan, koominikeeshinii, galaa qopheessuu, warra duulan kunuunsuu, nageenya kabachiisuufi buqqaatota deeggaruudhaan duultan hundi baga gammaddani!
በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና #የኢትዮጵያ ወዳጆች የ #ወደሀገርቤት እንግባ ጥሪን እንድትቀላቀሉ እንጋብዛለን።

1 ሚሊየን ሰዎች በሀገር ቤት በታኅሣሥ 29፣ 2014 ዓ.ም.

Itoophiyaanonni fi michuuwwan #Itoophiyaa guutuu addunyaatti argamtan waamicha #BiyyattiHaagallu jedhutti akka makamtan isin afeerra.

Mudde 29/2014 tti namoota miliyoona 1 gara biyyaatti.

Ethiopians and friends of #Ethiopia around the world, join the #GreatEthiopianHomeComing Challenge

1 million by January 7, 2022
ኢትዮጵያ ተስፋ መቁረጥን ራሱን ተስፋ አስቆርጣዋለች። የማያውቋት ተነሡባት። የሚያውቋት ተነሡላት። የማያውቋት ዘመቱባት፤ የሚያውቋት ዘመቱላት። ኢትዮጵያ ማለት ሲነኳት ማንም የማያውቀውን ኃይሏን የምታወጣ ሀገር ናት። እየሆነ ያለውም ይሄ ነው።
አርሶ አደሩን ማኅበረሰባችንን በመኸር ስብሰባ ለመደገፍ በዚህ ሳምንት ለተሠማራችሁ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና አስተማሪዎች በሙሉ አድናቆቴ ይድረሳችሁ። እንደ ሀገር በአንድነት ሆነን በጽናት ጉዟችንን እንቀጥላለን!

My appreciation to all high school students and teachers that are taking this week to support our farming communities with harvest. In unity, we will continue persevering as a nation!
TikTok and Fitness: The Rise of Wellness Trends on the Platform