Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
114K subscribers
5.11K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
ይኼ ጊዜ ችግሮች ተደራርበው የመጡበት የፈተና ጊዜ ነው። ፈተናው እስኪያልፍ ሁሉም ሰው መፈተኑ አይቀርም። ችግሮቻችን አፋጣኝ መፍትሄ አግኝተው ወደ መደበኛ ኑሮ እስክንመስ ሁላችንም አኗኗራችንን ለፈተና ጊዜ እንዲስማማ አድርገን መቆየት አለብን። እንደ ሰላሙ ጊዜ ነገሮች አልጋ በአልጋ እንዲሆኑ መጠበቅ የሰላሙን ጊዜ ያርቀዋል እንጂ ፈጽሞ አያቀርበውም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀውም የመከራውን ጊዜ ለማሳጠርና የመፍትሔውን ጊዜ ለማቅረብ ነው። ስለዚህ ዜጎች ወቅቱ እንደሚጠይቀው በመሆን፣ አዋጁ የሚያዝዛቸውን መመሪያዎች በማክበር፣ የሕግ አስከባሪ አካላት ሥራቸውን በቅልጥፍና እንዲያከናውኑ በመተባበር እና አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ሁሉም የበኩሉም ሚና እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ ለተሠዉ ጀግኖቻችን!!

ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር ናት፡፡ ልባም ልጆችዋ አጥር ሆነው የጋረዷት፣ ዋጋ ከፍለው ያደመቋት፣ ተቆጥሮ በማያልቅ መሥዋዕትነት ታፍራና ተከብራ የኖረች ሀገር ናት፡፡ የሩቁ ቢዘነጋን እንኳን፣ አምና ጥቅምት 24 ግፍ የተፈጸመባቸው ጀግኖቻችን ታሪክ ፈጽሞ የሚረሳ አይደለም፡፡ እያንዳንዳችን የጀግኖቹ ዕዳ አለብን፡፡ ዛሬ የቆምነው ለእኛ ሲሉ የግፍ ጽዋን በተጎነጩ ጀግኖቻችን አጥንት ላይ ነው፡፡ እነዚያ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች “ከወገኔ በፊት እኔ ልቅደም” ብለው ደማቸውን ለአፈር፣ ሥጋቸውን ለአሞራ ባይሰጡ ኖሮ የዛሬው ቀን ዛሬን ባልመሰለ ነበር፡፡

የሰሜን ዕዝ ሠራዊት የተደራጀው ከአንድ አካባቢ አልነበረም፡፡ አማራና ኦሮሞው፣ ሲዳማና ወላይታው፣ አፋርና ጋምቤላው፣ ጉራጌና ሐድያው ከሁሉም ብሔር ተውጣጥቶ ሀገር እንዲጠብቅ የተደራጀ ሠራዊት ነበር፡፡ ሀገሬን ብሎ ለሃያ ዓመታት ከቤቱና ካሳደገው ቀዬ ተነጥሎ ዱር እያደረ ድንበር ሲጠብቅ ኖሯል፡፡ ሠራዊቱ ለትግራይ ክልልና ለሕዝቡ ከደግነት ውጭ ክፉ ሆኖ አያውቅም። ጠላት ሲመጣ የሚመክት፣ አዝመራ ሲደርስ የሚያጭድ፣ በማኅበረሰባዊ ተግባራት ላይ የሚካፈል ነበር። በደምና በላቡ ለከፈለው ደግነት በምላሹ ከሽብር ቡድኑ ሕወሐት የተቀበለው ክህደት ነው።

ኢትዮጵያን ለመውረር የመጡ ጠላቶች እንደ ሽብር ቡድኑ ዋነኛ የጦር ቤዛችንን በመደብደብ አልጀመሩም፡፡ ዋና ዋና መኮንኖችን በመግደልና ከባድ መሣሪያዎቻችንን ዘርፈው አልተነሡም። የጦርነት ቅዱስ ባይኖርም ለጭካኔም ልክ አለው። በሽብር ቡድኑ ልክ ኢትዮጵያ ላይ የጨከነ የለም፡፡ ጥቅምት 24 ሠራዊቱ ላይ የክህደት ጥቃት ሲፈጸም የሞቱት እነዚያ ጀግኖች ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ እንደመሆናቸው የተፈጸመባቸው ግፍ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመ ግፍ ነው።

የሽብር ቡድኑ በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመው ጥቃት መሣሪያ ለመዝረፍ ብቻ የተደረገ ተራ ጥቃት አልነበረም፡፡ በተንኮል የተቀመመና በክፋት የሞላ መሆኑ የተለየ ያደርገዋል፡፡ የገዛ ጓዶቹን አስኮብልሎ በተኛበት ከመግደል ባለፈ ከሬሳው ላይ ልብሱን ገፍፎ የአውሬ ቀለብ እንዲሆን እርቃኑን ሜዳ ላይ ጥሎታል። ይኼን ሲያደርግ የሽብር ቡድኑ ዓላማ ሁለት ነው፡፡ አንደኛ ሠራዊቱ በሐፍረት በትር እየተቀጣ ሞራሉ እንዲላሽቅና የአቅመ ቢስነት ስሜት እንዲሰማው፡፡ ሁለተኛ ሠራዊቱ እርስ በእርስ እንዳይተማመንና “ክፉና ደጉን አብሮ ከተካፈሉኝ ጓዶቼ እንደዚህ ዓይነት ነውር ዛሬ ከተፈጸመብኝ ነገስ?” ብሎ እንዲጠራጠር ለማድረግ ታስቦ ነበር፡፡ ዳሩ ግን ሠራዊቱ እንደተጠበቀው አልሆነም፡፡

የወንድሞቹ ደም በከንቱ መፍሰስ ያንገበገበው ሠራዊት በፍጥነት ራሱን አደራጅቶ በሦስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የሽብር ቡድኑ ያደራጀውን ኃይል ወደ በርሃ እንዲበተን ማድረግ ችሏል፡፡ የቡድኑን ቁንጮ አመራሮች አብዛኞቹን ይዞ ለሕግ አስረክቧል፡፡ የተፈጸመበትን ክህደት በበቀል ሒሳብ ሳይሆን የሕግ ማስከበር መርሕን በተከተለ መንገድ ሲያከናውን ነበር፡፡ በጦርነት ውስጥ ለመርሕ መገዛት ቀላል አይደለም፡፡ ሠራዊታችን ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከሽብር ቡድኑ ጋር አያሌ ውጊያዎችን ሲያደርግ ብዙ ዋጋ ከፍሏል፡፡ በየጦር ውሎው በጀግንነት እየተዋጋ ለእናት ሀገሩ ተሠውቷል፡፡ ለሀገርና ለወገን ያለውን አጋርነት በንግግር ሳይሆን በተግባር አሳይቷል፡፡ አሁንም በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ነው፡፡

ዛሬ ሽብር ቡድኑ የተሰጠውን የጥሞና ጊዜ እንድ እድል ከመጠቀም ይልቅ እንደ ድል ወሰደው። በአማራና በአፋር ክልል በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የግፍ በትሩን ቀጥሎበታል፡፡ የጥፋት አጋሩ ሸኔም በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ ልዩ ልዩ አደጋዎችን እየጣለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን ረፍት እየነሣ ነው፡፡ ሌሎችም የጥፋት ኃይሎች ከውስጥም ከውጭም ወኪሎቻቸውን አስተባብረው በሙሉ ዐቅማቸው ኢትዮጵያ ላይ መዝመታቸውን ገፍተውበታል፡፡

ሠራዊታችን ብቻውን ተጋፍጦ የድል ዜና እንዲያበስረን መጠበቅም ሞኝነት ነው፡፡ ጠላቶቻችን ተባብረው የደቀኑብን አደጋ ሁላችንም ተባብረን ካልመከትነው ድል የማይታሰብ ነው፡፡ የጠላቶቻችን ኅብረት ለፕሮፓጋንዳ የተፈበረከ ጉዳይ አይደለም፡፡ እውነት ነው፡፡ እነዚህ ኃይሎች ዓላማቸው ግልጽ ነው፡፡ ብረት ያነሡት ሀገር ለማፍረስ እንጂ ሀገር ለመገንባት አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን ስም በክፉ የሚያብጠለጥሉ፣ ነገ የሊቢያና የሶርያን እጣ ሊያስታቅፉን እንዲመቻቸው የፈጠሩት ዘዴ መሆኑን ልናውቅ ይገባል፡፡ ጠላቶቻችን በዚህ ደረጃ ሲተባበሩብን እኛ አንድ የማንሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ የወንድምና የእኅቶቹ ጥቃት የሚያንገበግበው ሁሉ ጣት ከመጠቆም ወጥቶ ሀገር የማዳን ፍላጎቱን በተግባር መግለጥ አለበት፡፡

ወደፊት ታሪክ ፍርዱን ይሰጣል፡፡ ፈሪውም በፈሪነቱ፣ ሴረኛውም በሴረኛነቱ እንደየግብሩ ይመዘገባል፡፡ የሽብር ቡድኑን ትውልድ በክህደት ሲያስታውሳቸው እንደሚኖር ግልጽ ነው፡፡ በተቃራኒው በግፍ የተሠውት የሰሜን ዕዝ አባላትን ጨምሮ ለሀገር የሚዋደቁ ጀግኖች ስማቸው በወርቅ ይጻፋል፡፡

ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ ለተሠዉ ጀግኖቻችን!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጥቅምት 24፣ 2014 ዓ.ም
ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ ለተሠዉ ጀግኖቻችን!

Kabajni gootota keenya Itoophiyaaf jedhanii aarsaa ta'aniif!
A statement with respect to the Joint Investigation Team Report of the EHRC and UNOHCHR
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ ለተሠዉ ጀግኖቻችን!

Kabajni gootota keenya Itoophiyaaf jedhanii aarsaa ta'aniif!
የመጨረሻው ከባዱ ምጥ ልጁ የሚወለድበት ነው። ይህ ፈታኝ ጊዜም ጀግኖች የሚወለዱበት ነው።

የኢትዮጵያ ልጆች ከጫፍ እስከጫፍ ተነሥተዋል። ፈተናዎቹ አጠንክረውናል። ፈታኞቻችን ሌሎች መንገዶችን አሳይተውናል።

ፊታቸውን ካዞሩብን ወዳጆች እጥፍ የቁርጥ ቀን ወዳጆች አግኝተናል።

የቅጠሎች መሰብሰብ ዋርካ አያደርጋቸውም። የዋርካዎች መሰብሰብ ግን ደኑን የማይደፈር እያደረገው ነው።

የሚከፈል መሥዋዕትነት አለ። ያ መሥዋዕትነት ግን ኢትዮጵያን ዋጅቶ በዐለት ላይ ይተክላታል።


Ciniinsuun inni dhumaa ulfaataan isa mucaan ittiin dhalatudha. Yeroon qorumsaa kunis kan gootonni ittiin dhalatanidha.

Ijoolleen Itoophiyaa gamaa gamanaa ka'aniiru. Qorumsoonni nu cimsaniiru. Warri nuqoran daandiiwwan kanbiroo nu agarsiisaniiru.

Michuuwwan fuula nurraa galagalfatan caalaa michuuwwan gaafa xiiqii dachaa arganneerra.

Baalonni walittiqabamuun qilxuu isaan hin taasisu. Walittiqabamuun qilxuuwwanii garuu bosonicha akka hin tuqamne gochaa jira.

Aarsaan kanfalamu jira. Aarsaan sun garuu Itoophiyaa baraaree kattaarra dhaaba.
የምንታወክበትን ወቅት ሳንታወክ ማለፍ የብሔራዊ ጽናት ምልክት ነው። በብዙ አቅጣጫዎች እየተፈተንን ነው። ፈተናውን የምናልፍበት ጥንካሬያችን የጀመርነውን ጉዞ እውን ለማድረግ ካለን የጋራ ፍላጎት የሚመነጭ ነው። ወደ ኋላ የሚጎትተን ቢበዛም በብርቱ ክንድ፣ በጸና ልቡና፣ ለድል በሚገሠግሥ መንፈስ #የኢትዮጵያን አሸናፊነት እናበሥራለን።

Yeroo itti raafamnutti utuu hin raafamiin darbuun mallattoo cimina biyyoolessaati. Kallattiiwwan baay'eedhaan qoramaa jirra. Jabinni keenya qormaaticha ittiin darbinu fedhii waloo imala jalqabne dhugoomsuuf qabnurraa madda. Wanti duubatti nuharkisu heddummatus irree jabaadhaan, qalbii kutataafi miira injifannoof fuulduratti adeemuun injifattummaa #Itoophiyaa ni labsina.

Overcoming a turbulent period is a mark of national resilience. While we are being tested on many fronts, our collective will to realize the path we have embarked upon has strengthened us. Despite all attempting to hold us back, let’s continue moving forward in unity #Ethiopia.
ከስዊድኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስቴፈን ሎቨን ጋር የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው በሀገራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ የስልክ ውይይት አድርገናል፡፡ ስዊድን የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ ለመደገፍ ስለምታደርገው አስተዋጽኦ አመሰግናለሁ፡፡

Ministira Muummee Siwiidin, Isteeven Lofven waliin dhimmoota waloo biyyaafi naannawaaf faayidaa qaban irratti marii bilbilaa bu'a qabeessa ta'e gooneerra. Siwiidin adeemsa jijjiirama Itoophiyaa deeggaruuf gumaacha taasistuuf nan galateeffadha.


Held a fruitful call discussion with Prime Minister Stefan Löfven on various bilateral and regional issues of mutual interest. I greatly appreciate Sweden for the lasting contribution to Ethiopia's reform journey.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ አትበተንም ጠላቶቿን አሸንፋ የአፍሪካ ፈርጥና ምሳሌ ትሆናለች"
በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መንግሥት በሚፈተን ግን በማይቀለበስ የለውጥ ጉዞ ላይ ነው። መንግሥት ጊዜያዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የልማት ግቦችን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር ገንቢ በሆነ መልኩ ለመሥራት ምንጊዜም ዝግጁ ነው። መሰናክሎች ያስተምሩናል እንጂ አያስቆሙንም። በያዝነው የለውጥ ጎዳና ወደ ፊት ለመጓዝ ቁርጠኞች ነን።

The democratically elected sovereign government of Ethiopia stands ready to work constructively with friends of Ethiopia in addressing temporal challenges & realizing dev’t goals per the reforms journey started. We remain committed to progress albeit the obstacles encountered.
አንዳንዶች ጩኸታችንን ሊቀሙ እየሞከሩ ነው። በኢትዮጵያዊነታችን ላይ የተመሠረተውን ክብርና አንድነት መቼም ሊነኩት አይቻላቸውም። እኛ የኮራን ኢትዮጵያውያን ነን። የኮራን አፍሪካውያን ነን። በከፍታ፣ በጽናትና በአንድነት ለኢትዮጵያ የምንቆም።

Some may continue trying to strip us off truth, context and recent realities, yet none can snatch away our collective dignity and unity as proud Ethiopians - as proud Africans. Stand tall, stand firm and stand together for #Ethiopia!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“የሕልውና ጥሪ እና ሀገርን የማዳን ርብርብ”
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የስልክ ውይይት አድርገናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ለኢትዮጵያ ስላሳዩት ልባዊ ወዳጅነት እና ድጋፍ ጥልቅ ምሥጋና አቀርባለሁ።

Productive phone call with Prime Minister of Canada @JustinTrudeau on bilateral issues. I would like to thank Prime Minister Justin for his sincere friendship and support to Ethiopia.
ውቢቷ #ኢትዮጵያ ብዙም የማይነገርላት።

ልጆቿ በአንድ ልብ ኃይላቸውን አንድ አድርገው የሚታገሉላት #ኢትዮጵያ

#በጽናትትገሠግሣለች

The beautiful #Ethiopia one is rarely told about.

The #Ethiopia that her children will continue striving for as a united force.

#ResilientlyOnwards
ዉድ ወንድሜ ፕሬዚደንት ኡኹሩ ኬንያታ ወደ ሁለተኛዉ ቤትዎ እንኳን ደህና መጡ።
Obboleessakoo jaalatamaa, Uhuruu Keeniyaattaa baga nagaan gara mana keessan lammaffaa dhuftani.

I welcome my dear brother President Uhuru Kenyatta to his second home.
How to Record Hands-Free on Snapchat