Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
114K subscribers
5.1K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
ታሪክ ሠርታችኋል

500 ሚልዮን ዛፎችን በመትከል የራሳችንን ሪከርድ እንድንሰብር የቀረበውን ጥሪ ተቀብላችሁ የወጣችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል። አረንጓዴ ታሪክ ሠርታችኋል። አረንጓዴ ታሪክ ጽፋችኋል።

የተዛባ አየር፣ የተራቆተ ምድር ለትውልድ አናወርስም ብላችሁ፤ ጎሕ ሳይቀድ ወደ ተራሮችና ሸለቆዎች፣ ወደ ሜዳዎችና ሸንተረሮች ተሠማርታችሁ 566 ሚልዮን ዛፎች ተክላችኋል። ሪከርዳችሁን ሰብራችኋል።

በሁሉም ክልሎች፣ ዞኖችና ወረዳዎች ዛፎች ተተክለዋል። ከ9 ሺ በላይ የተለዩ ቦታዎች ተዘጋጅተው ነበር። ከ3600 በላይ የሚዲያ ባለሞያዎች በመላ ሀገሪቱ ተሠማርተው ነበር። የቴሌና የግብርና ባለሞያዎች የመረጃ አያያዙ ዘመናዊ እንዲሆን ሠርተዋል። የአዲስ አበባ ታክሲዎች ነጻ ትራንስፖርት ለችግኝ ተካዮች ተሰጥተዋል። ሕጻናት፣ እናቶች፣ አባቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ በነቂስ ወጥተው ተክለዋል። በኢትዮጵያውያን አረንጓዴ ታሪክ ተሠርቷል።

ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የማንሰብረው ሪከርድ የለም።
ዛሬ ከፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ጋር በሁለትዮሽ እና በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች፣ እንዲሁም በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ሰላም ለማምጣት በሚቻልበት መንገድ ላይ በስልክ ተወያይተናል።

Har'a Pirezdaanti Zeleneskii waliin dhimmota garlameefi dhimmoota waloo idil-addunyaa irratti, akkasumas haala Raashiyaafi Yuukreen gidduutti nagaa buusuun danda'amu irratti bilbilaan marii'anneerra.

I held a phone call with President Zelensky today to discuss bilateral and international matters of mutual interest as well as the means and ways of bringing peace between Ukraine and Russia.
Twitter Analytics: Measuring and Optimizing Your Social Media Impact