Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
113K subscribers
5.1K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
እጅ ያልነካቸው የወንጪ እና ደንዲ ያማሩ የእሳተ ገሞራ ሐይቆች በመጨረሻ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ዛሬ ሦስተኛውን ‹የገበታ ለሀገር› ፕሮጀክት በወንጪ ከተማ አስጀምረናል። ይህ ፕሮጀክት መንገዶችን እና የኤሌክትሪክ ኃይልን ያስገኛል። የቴሌኮም አገልግሎቶችን በማሻሻል የግል ባለሀብቱ በኢኮ ቱሪዝም ዘርፍ ሙዐለ ንዋይ እንዲያፈስ ያስችላል፡፡

Haroowwan voolkaanoo miidhagaa Wanciifi Daandii dhumarratti xiyyeeffannoo maluuf argataniiru. Har'a Wanciitti piroojektii "Maaddii Biyyaaf" isa 3ffa jalqabsiifneerra. Piroojektiin kun daandiiwwanifi elektiriikii of keessaa qaba. Tajaajila telekoomii guddisuudhaan abbootiin qabeenyaa dhuunfaa damee ekkoo tuuriizimiirratti akka hojjetan dandeessisa.

The pristine volcanic lakes of Wenchi and Dendi have finally been given the attention they deserve. Today we launched the third ‘DineForEthiopia’ project in Wenchi which will bring in roads, electricity and enhance telecom services to enable private sector investments in eco tourism.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Wanciifi-Daandii ekkoo tuuriizimii Piroojektii
ዛሬ ጠዋት ከብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር በነበረን ስብሰባ ወቅት፣ሠራዊታችን የሠላም ጠባቂ እና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚያስከብር በመሆኑ የሚሰማኝን ኩራት ገልጫለሁ። ስነ ምግባርን እና ሙያተኝነትን የማጠናከር እና በየትኛውም የሕግ ማስከበር ሥራ የመከላከያ ሠራዊታችንን እሴቶች የማይወክል ተግባር የሚፈጽሙትን ተጠያቂ ማድረግ፣ በአግባቡ ኃላፊነታቸውን የሚወጡትን መሸለም እንደሚገባ አሳስቤያለሁ። የተጠያቂነት እና የስነ ምግባር ክፍተቶች በተገቢው ስርዓት ርምጃ የሚወሰድባቸው ይሆናል።

In my meeting this morning with the leadership of the Ethiopian National Defense Forces, I expressed pride in our forces as guardians of peace and protectors of sovereignty. I also cautioned them on the need to strengthen discipline and professionalism, holding accountable those that undertake deeds in any operation which do not represent the ENDF values and rewarding those that do. Accountability and disciplinary gaps will be addressed through the appropriate channels.
ሃምሳ ሦስተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የገንዘብ፣ ዕቅድ እና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሮች ጉባዔ አጀንዳ ወቅታዊ እና ተገቢ ነው፡፡ በዓለማችን እየጨመረ ከመጣው ተፈጥሯዊ እና ሰብአዊ ነውጥ ጋር በተያያዘ፣ ፈጠራ የታከለባቸው ምላሾች ያስፈልጉናል። አፍሪካ የኮቪድ19ኝን ቀውስ ተጋፍጣ መፍትሔዎችን ለመቅረጽ እና ተግባራዊ ለማድረግ ያሳየችውን ዐቅም እና ዝግጁነት የሚደነቅ ነው፡፡ ቀጥለን በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በአየር ንብረት ለውጥ ተኮር ኢኮኖሚ እና ተቋማዊ ማሕቀፎችን በማብቃት ላይ ልናተኩር ይገባል። ይህንንም እውን ማድረግ እንደሚቻል በሀገራችን ያስጀመርናቸው ምዕራፎች ያመላክታሉ። አህጉራችን የዓለም አቀፍ ምጣኔ ሀብት ዐምድ መሆኗ የማይቀር ነው!
How to Change Teams Background