Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
113K subscribers
5.09K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋን ዛሬ በጽሕፈት ቤታችን አግኝቼ ሰፊ ውይይት አድርገናል። የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የትብብር አድማስ በማስፋት ለኢኮኖሚ እድገታችን በኮንሴሽናል ፋይናንስ፣ በአለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በኩል ጠንካራ የኢንቨስትመንት ፋይናንስ አቅርቦት እና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችንን የሚደግፍ የዘለቀ አስተዋፅዖ ይኖረዋል።

Pleased to receive World Bank President Ajay Banga today. The World Bank will be instrumental to our economic growth in expanding its scope of partnership with Ethiopia through increased concessional financing, robust investment financing through IFC and support for our homegrown economic reform agenda.
ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህዎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ያስገኙ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ገንብታ ወደ ስራ አስገብታለች። የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮችንም ገንብተን በስራ ላይ እንገኛለን።

ከአለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ ጋር በመሆን ዛሬ ጠዋት በአንደኛው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በምርት ስራ ላይ ካሉ ኢንዱስትሪዎቻችን ሁለቱን አብረን ጎብኝተናል። ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም ያላት ሀገር ብቻ ሳትሆን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መዋእለ ነዋይ ለማፍሰስ ለሚሹ ሁሉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች ነው።

Ethiopia has built and operationalized 13 industry parks that have enabled full time employment for thousands. We have also built and operationalized agro-processing industry parks.

Together with World Bank President Ajay Banga we visited two industries actively producing in one of our nationwide industry parks. Ethiopia has great potential and is creating a conducive environment for more investments in various industries.
የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን ተቀብዬ አነጋግሪያለው። ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች:: በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ አቋምም አላት።

I welcome to #Ethiopia Hayashi Yoshimasa, Foreign Minister of Japan. Ethiopia attaches great importance to its relations with Japan and remains committed to cooperate on issues of mutual interest.
ዛሬ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትን በጽ/ቤታችን ተቀብያለሁ። የጋራ ቀጠናዊ ጥቅም ያለን ጎረቤቶች እንደመሆናችን መጠን ትብብራችንን ያለማቋረጥ እናጠናክራለን።

I received today President Salva Kiir Mayardit. As neighbors with common regional interests, we will continuously strengthen our cooperation.
የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያ ግንኙነት ከስድስት ዐሠርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ነው። ከደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ተወያይተናል።

Relations between Ethiopia and South Korea span over six decades. Received the Foreign Minister of South Korea, Park Jin today for a discussion on various issues.
ዛሬ ጠዋት የኢትዮጵያ ትልቁ ኤሊት ኃይል የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በመገኘቴ ክብር ይሰማኛል። ይህ ኃይል ሁለት ዓላማዎች አሉት:- 1)ውጊያ ማስቀረት እና 2)ገፍቶ ከመጣ ደግሞ ውጊያን የመጨረስ ተልዕኮ ያለው ነው:: እንዲህ ያለው ኃይል ይህቺን ትልቅ ሀገር አጽንቶ ለትውልድ ያሻግራል።

I am honored to preside over the graduation ceremony of Ethiopia’s largest elite force this morning. This force is tasked with the dual objectives of stopping battles from occurring and if pushed into one, then finishing ones that have been started. Our elite forces will sustain and handover to coming generations a resilient and great Ethiopia.
The Benefits of Using a YT Audio to MP3 Converter