Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
112K subscribers
5.01K photos
248 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
በአማራ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በመላው የክልሉ አካባቢዎች በብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ከሁሉም ዞኖች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር በክልሉ የገጠሙ ቁልፍ ጉዳዮችን አስመልክቶ ውይይት አድርገናል።
በቀረቡ በርካታ ጉዳዮች ላይ ምላሽ በመስጠት ለጋራ አላማ የጋራ ጥረት የማድረግን አስፈላጊነት በአፅንዖት አንስተናል።

Following region-wide discussions held in the Amhara Region, led by PP Executive Members, I have convened representatives from all zones of the region this morning to address critical current issues facing the region. Providing responses on a number of issues, we have underscored the importance of uniting efforts for a common purpose.
በፈጠራ የታገዙ መፍትሄዎችን ለማስገኘት በሶስትዮሽ ትብብር ይፋ የተደረገው በኢትዮዽያ በግብርና፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በታዳሽ ኃይል፣ በዲጂታይዜሽን የልህቀት ማዕከላትን የመመስረት ስራ የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን እና የገጠር ነዋሪዎችን ሕይወት ለማሻሻል ልዩ ዕድል ይዞ መጥቷል። ለቻይና መንግስት እና ለዩኤንአይዲኦ በዚህ እጅግ አስፈላጊ ሃሳብ ላይ በመተባበራቸው ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ። የዩኤንአይዲኦ ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ለኢትዮጵያ የልማት ስራ ላላቸው የፀና ድጋፍ በተለይ ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ።

The Joint Declaration for Tripartite Cooperation on the Establishment of Centers of Excellence in Ethiopia, focusing on agriculture, agro-industries, renewable energy, and digitization, presents a unique opportunity for Ethiopia to enhance the livelihoods of farmers and rural communities through innovative solutions provided by these centers. I extend my gratitude to the Government of China and UNIDO for their pivotal role in facilitating this initiative. And special thanks to UNIDO’s Director General Gerd Muller for your continued commitment to #Ethiopia’s development.
የኢትዮዽያ ኢንቬስትመንት ሆልዲንግስ ቦርድ ኢትዮ ቴሌኮም ህዝባዊ ለመሆን ያለውን ዝግጁነት እና የካፒታል ማርኬት ባለስልጣን በኢትዮዽያ የካፒታል ገበያን ወደስራ በማስገባት ላይ የደረሰበትን ደረጃ ገምግሟል፡፡ በኢትዮዽያ የድርሻ ገበያ እና ልውውጥ(ስቶክ ማርኬት ኤንድ ኤክስቼንጅ) መጀመር ኢትዮጵያ የእድገት ትልሟ እውን እንዲሆን አዳዲስ ካፒታል በመሳብ ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል። ይኽ ለሀገራችን አጓጊ አዲስ ምዕራፍ ነው።

The board of Ethiopian Investment Holdings met today to assess Ethio Telecom’s readiness to go public and to evaluate the Capital Markets Authority's progress in operationalizing the capital markets. The introduction of a stock market and exchange in Ethiopia is poised to be a game-changer, supporting Ethiopia in achieving its growth aspirations and attracting new capital. This marks an exciting chapter for the nation.
How to Change Teams Background