Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
112K subscribers
4.94K photos
245 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
ሕይወት ተፈራ "ምንትዋብ" የተሰኘ ታሪካዊ ልቦለድ አቅርባልናለች። እቴጌ ምንትዋብ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተነሡ ኃያላን ሴት መሪዎች አንዷ ናት። የሕይወት መጽሐፍ ያረፈበት መቼት ለዛሬው የሀገር ግንባታ ጉዟችን ብዙ ትምህርት ይሰጠናል። ከፍቅሩ፣ ከጠቡ፣ ከሽኩቻው፣ አንዱ ሲገነባ ሌላው ለማፍረስ ከሚጥረው፣ አንዱ ለሀገር ሌላው ለመንደር ከሚያስበው፤ ብዙ እንማርበታለን። ሕይወት ብዕርሽ አይንጠፍ።
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የከተማ መኖሪያ ቤት እጥረትን ለማቃለል የሚያደርጋቸውን ጥረቶች በማየቴ ደስተኛ ነኝ። በስድስት ወራት ውስጥ በ3 ሄክታር መሬት ላይ በ16 ሕንፃዎች 500 ቤቶችን በ3 ቢሊየን ብር ገንብተዋል። የከተማ የመኖሪያ ፍላጎትን ለማሟላት፣ መንግሥት እንደዚህ ያሉ ተቋማቶን ማጠናከሩን ይቀጥላል።

Pleased to see the progress of the Federal Housing Corporation’s efforts in addressing urban housing shortages. In six months 500 houses have been built in 16 blocks on 3 hectares of land at a cost of Birr 3 billion. The government will continue developing such facilities to meet urban housing needs.
የዛሬ ዐሥር ዓመት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ተወጥኖ ተጀመረ። ከብዙ የሥራ መዘግየትና መጓተት በኋላ፣ የዛሬ ሦስት ዓመት ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት ታልሞ ሥራው ቀጠለ። ከ 14 እስከ 17 ፎቅ ያሏቸውን 6 ሕንጻዎች ይዞ፣ በ7,550 ሜትር ስኴር መሬት ላይ ያረፈው አዲሱ የኢመደኤ ዋና መሥሪያ ቤት፣ የሰላም ሚኒስቴርን፣ የአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ ማዕከልን፣ የፋይንስ ኢንተሌጀንስ ማዕከልን ቢሮዎች ይዟል። ከመሠረተ ልማት በተጨማሪ፣ የኢመደኤ ዋና መሥሪያ ቤት መሪ አፍሪካዊ የሳይበር ተቋምን እውን የማድረግ ራእይን የያዘ ነው። ኢመደኤ በመላው ሀገሪቱ ያሉ ተቋማት ተምሳሌትነቱን ሊከተሉ የሚገባ ነው። ምንም ዓይነት ተግዳሮት ቢገጥመን፣ ሀገራዊ የብልጽግና ሕልማችን ሳይደናቀፍ ይቀጥላል።
How to Save Live Photo as Video