Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
112K subscribers
4.92K photos
245 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ውስጥ እያካሄደ ያለውን ለውጥ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ጋር ለመጎብኘት በመቻሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡ በባዮሴፍቲ እና ባዮ ሴኪዩሪቲ ላይ ባተኮረ ዘመናዊ የአቪዬሽን እየተገነባ ያለው መሠረተ ልማት፤ አዲስ ተርሚናል ፣ የክብር እንግዳ መቀበያ ሳሎን፣ የቢዝነስ ላውንጅ እና ሌሎች ተቋማትን ይዟል፡፡

Pleased to witness with the Council of Ministers the transformation taking place within Bole International Airport by the Ethiopian Airlines Group. A modern aviation infrastructure has taken shape featuring a new terminal, VIP terminal section, business lounge and other facilities with an overall focus on biosafety and biosecurity.
የኢትዮጵያ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል። ከተሠራ የማይመጣ ውጤት የለም። 🇪🇹

Gareen Biyyaalessaa Itoophiyaa Waancaa Afrikaatiif darbuusaatiin gammachuu guddaan natti dhagahameera. Hojjetamnaan bu'aan hin dhufne hin jiru. 🇪🇹
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ወለጋ ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እናወግዛለን፡፡ የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን ለሟች ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እንገልጻለን፡፡ ዓለማችን በወረርሽኝ ተጨንቃ መፍትሔ በምትፈልግበት በዚህ ሰዓት፣ ሆን ብለው በሰዎች ላይ መከራና ስቃይ የሚጨምሩ ግለሰቦች እና ቡድኖች በምንፈልጋት ኢትዮጵያ ውስጥ ስፍራ የላቸውም። ጠላቶቻችን በውስጥና በውጭ ተደራጅተው ንጽሐን ዜጎቻችንን በመግደል የጀመርነውን ጉዞ ለማሸማቀቅና ከመንገዳችን ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ ነው። መሥዋዕትነት እየከፈልንም ቢሆን የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክረን ጉዟችንን እንቀጥላለን። በሁሉም ቦታ በደርሰው ጥቃት አጸፋ እርምጃ በክልልና በፈዴራል መንግሥት ቅንጅት እየተወሰደ ይገኛል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ጥፋት ኃይሎች ወጥመድ ላለመውደቅ በማስተዋል እየተጓዘ፤ በእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ከመንግሥት ጋር ተባበሮ ጥፋተኞችን ወደ ሕግ ለማቅረብ እና እንደዚህ ዓይነት ግድያዎች ፈጽመው እንዲቆሙ በትብብር ልንሠራ ይገባል። ኢትዮጵያ በመሥዋዕትነት የቆመች፤ በመሥዋዕትነት የምትቀጥል ሀገር ናት። በትብብርና በአንድነት መንፈስ የኢትዮጵያን ጠላቶች ደግመው እንዳይነሡ አድርገን ማጥፋት አለብን።
ደመና የማዝነብ ቴክኖሎጂ የሙከራ ትግበራ በስኬታማነት ተጠናቅቋል። ይህም ሀገራችን ከኃይል ማመንጫ እና መስኖ አንጻር የምትሠራቸውን ሥራዎች ተጨማሪ ዝናብ በማዝነብ መደገፍ እንደሚቻል ያመላክታል።
ሀገርን ለማዘመን የሚደረጉ ይህን የመሳሰሉ ጥረቶች ላይ ማተኮር እንዲቻሎ አጥፊዎችን ለማጥፋትና ጥፋትን ለማስቆም መላው ሕዝባችን ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር መሥራት አለበት ። የሀገራችን ዕድገት የአፍሪካም ዕድገት ነው። በሙከራ ሂደቱ የተሳተፋችሁ አካላት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

The successful completion of the cloud-seeding demonstration implies that our country's efforts in hydropower generation and irrigation will be supported by more rain. All Ethiopians are expected to work with law enforcement agencies to thwart the plans of criminals who want us to give up our dreams of modernizing our country. The growth of our Ethiopia is the growth of our continent. Thank you all who took part in the successful trial.
How to Save Live Photo as Video