Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
110K subscribers
4.83K photos
240 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
ዛሬ ጠዋት ከብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር በነበረን ስብሰባ ወቅት፣ሠራዊታችን የሠላም ጠባቂ እና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚያስከብር በመሆኑ የሚሰማኝን ኩራት ገልጫለሁ። ስነ ምግባርን እና ሙያተኝነትን የማጠናከር እና በየትኛውም የሕግ ማስከበር ሥራ የመከላከያ ሠራዊታችንን እሴቶች የማይወክል ተግባር የሚፈጽሙትን ተጠያቂ ማድረግ፣ በአግባቡ ኃላፊነታቸውን የሚወጡትን መሸለም እንደሚገባ አሳስቤያለሁ። የተጠያቂነት እና የስነ ምግባር ክፍተቶች በተገቢው ስርዓት ርምጃ የሚወሰድባቸው ይሆናል።

In my meeting this morning with the leadership of the Ethiopian National Defense Forces, I expressed pride in our forces as guardians of peace and protectors of sovereignty. I also cautioned them on the need to strengthen discipline and professionalism, holding accountable those that undertake deeds in any operation which do not represent the ENDF values and rewarding those that do. Accountability and disciplinary gaps will be addressed through the appropriate channels.
ሃምሳ ሦስተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የገንዘብ፣ ዕቅድ እና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሮች ጉባዔ አጀንዳ ወቅታዊ እና ተገቢ ነው፡፡ በዓለማችን እየጨመረ ከመጣው ተፈጥሯዊ እና ሰብአዊ ነውጥ ጋር በተያያዘ፣ ፈጠራ የታከለባቸው ምላሾች ያስፈልጉናል። አፍሪካ የኮቪድ19ኝን ቀውስ ተጋፍጣ መፍትሔዎችን ለመቅረጽ እና ተግባራዊ ለማድረግ ያሳየችውን ዐቅም እና ዝግጁነት የሚደነቅ ነው፡፡ ቀጥለን በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በአየር ንብረት ለውጥ ተኮር ኢኮኖሚ እና ተቋማዊ ማሕቀፎችን በማብቃት ላይ ልናተኩር ይገባል። ይህንንም እውን ማድረግ እንደሚቻል በሀገራችን ያስጀመርናቸው ምዕራፎች ያመላክታሉ። አህጉራችን የዓለም አቀፍ ምጣኔ ሀብት ዐምድ መሆኗ የማይቀር ነው!
On Discussions with President Isaias Afwerki
መጋቢት 17፤ 2013

በጥቅምት 25፣ 2013 በሕወሐት ውስጥ የተሰባሰበው የወንጀል ቡድን፣ በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የከሸፈ ክህደት ፈጽሟል። በዚህም ሀገርን ወደ ሁከት በመምራት ሥልጣንን ለመያዝ መሞከሩ ይታወሳል። የሀገሪቱ ትልልቅ የጦር መሣሪያ ማከማቻዎች በሚገኙበት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙ እና የመከላከያ ሠራዊታችንን አባላት ያለ ርኅራኄ መግደሉ እና ማፈኑ የፌዴራል መንግሥት ሳይፈልግ ወታደራዊ ርምጃ እንዲወስድ አስገድዶታል።

በሰሜን እዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የሕወሐት ወንጀለኛ ቡድን በባሕር ዳር እና በጎንደር ከተሞች ላይ ሮኬቶችን መተኮሱ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይም በኤርትራ ላይ ተደጋጋሚ ሮኬቶችን ተኩሷል። ይህም የኤርትራን መንግሥት የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ በመግባት ከተጨማሪ ጥቃቶች ራሱን እንዲከላከል እና ብሔራዊ ደኅንነቱን እንዲጠብቅ አነሣሥቶታል፡፡

መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ አሥመራ ተጉዤ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ባደረግነው ውይይት፣ የኤርትራ መንግሥት ጦሩን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማምቷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት ወዲያውኑ ተክቶ የድንበር አካባቢዎችን ይጠብቃል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው እና በኢኮኖሚ ትብብር ፍላጎታቸው ላይ አብረው መሥራታቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ በ2010 ዓ.ም. በተጀመረው መሠረት በሁለቱ ሀገራት መካከል በመተማመን መንፈስ መልካም የጉርብትና ግንኙነታችንን መገንባታችንን እንቀጥላለን፡፡ በተለይም፣ በትግራይ ክልል እና ከድንበር ማዶ ባሉ ኤርትራውያን ወገኖቻችን መካከል በመተማመን ላየ የተመሠረተ ግንኙነትን መመለስ በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡
//
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የማዳጋስካር አቻውን 4 ለ0 አሸንፏል። በዚህም ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ዕድሉን አስፍቷል። ከተለያዩ አካባቢዎች እና ቡድኖች የመጡ ተጨዋቾች በአንድ ዓላማ ተጫውተው ያስገኙት ድል ትልቅ አርአያነት አለው። በቀጣዩ ጨዋታቸው መልካሙን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ።

Gareen biyyaalessaa kubbaa miilaa Itoophiyaa gitasaa Maadagaaskaar 4 fi 0 dhaan moo'ateera. Kanaanis carraasaa Waancaa Afrikaaf darbuu bal'ifateera. Taphattoonni bakka garaagaraafi gareewwan addaddaarraa dbufan kaayyoo tokkoof taphatanii injifannoon argamsiisan fakkeenyummaa kan qabudha. Taphasaanii itti aanuun milkaa'inan hawwaafi.
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የማምረት ዐቅሙን አጠናክሮ በዘላቂነት የሀገርን ሉዐላዊነትን ማስጠበቅ በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኝ ሪፎርም መጀመሩ ይታወቃል:: የተጀመረው ሪፎርም ትልቅ መሠረት እየጣለ መሆኑንን ዛሬ ሆሚቾ የአሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪን በመጎብኘት አይተናል:: መከላከያ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን በማምረት በዚህም የራሱን ቁመና አጠናክሮ ወትሮ ዝግጁነቱን በማሳደግ፣ በምርምር የሚልቅበት መሠረታዊ ሪፎርም መጀመሩን አይቻለሁ:: ይሄን አጠናክረን በመቀጠል መከላከያችን ሁለንተናዊ የተቋም ቁመና እንዲኖረው ቀጣይ ስራዎች ይሰራሉ::

It is known that the Ethiopian National Defense Forces have begun to reform and strengthen their production capacity to maintain our country's sovereignty in a sustainable manner. We witnessed that today as we visited Homicho Ammunition Engineering Industry. The ENDF’s capacity to manufacture international standard products and strengthen its readiness based on adequate research is evident. We will continue to build on these efforts.
Guide on How to Download Instagram Videos Effortlessly