Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
114K subscribers
5.11K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
የዘመናት ዕዳ አለብን። ያላከበርናቸው አያሌ ኢትዮጵያውያን አሉ። እጄ አመድ አፋሽ ነው እያሉ የሚኖሩ። አንዳንዱ ችግራችን ከምርቃታቸው ባለማግኘታችን ሊሆን ይችላል። ይሄንን የትውልድ ዕዳ መክፈል ጀምረናል።
ዛሬ በሙዚቃ፣ በድርሰት፣ በቴአትርና በሥዕል ሞያ ያገለገሉትን አንጋፋዎች ዛሬ አክብረን ሸልመናል። ኢትዮጵያን ስላገለገላችሁ፣ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያን ስላገለገላችሁ፣ ኢትዮጵያ ታመሰግናችኋለች።

Waan Itoophiyaa tajaajiltaniif Itoophiyaan isin galateeffatti.
ዜጎች ተገቢውን የጤና አገልግሎት ያገኙ ዘንድ ተደራሽነቱን ማስፋት በእጅጉ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው። ዛሬ ጠዋት የሮሀ የሕክምና ማዕከል ሰፊ ፕሮጀክት የግንባታ ሥራ መጀመሩ፣ ለዚሁ ቀዳሚ ተግባር የተሰጠውን ትኩረት ያመላክታል። ተጨማሪ 1,200 አልጋዎችን የሚኖሯቸውን 5 ሆስፒታሎች የሚያካትተው የሕክምና ማዕከል ተገንብቶ ሲጠናቀቅ፣ ኢትዮጵያ በሕክምና ቱሪዝም በኩልም ተፈላጊ እንድትሆን ያደርጋታል።

Advancing healthcare for citizens is a critical priority. The Roha Medical center mega project construction launch this morning demonstrates commitment to this priority. With 5 hospitals of more 1,200 beds, when completed the medical center will enable Ethiopia to become a medical tourism hotspot as well.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሮሀ የሕክምና ማዕከል
Roha Medical Center
Congratulations to my brother President Ismail Omar Guelleh on your reelection. #Ethiopia wishes you and the great people of Djibouti prosperity and remains a constant partner and neighbor.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በኅብረት ጸንተን፣ ቆርጠን ከሠራን፣ ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ በእያንዳንዳችን እጅ ነው::
#የብልጽግናራእይ
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ።

Hordoftoota Amantaa Islaamaa hunda, baga baatii Ramadaanaa guddichaan nagaan isin gahe.

I wish all followers of Islam a blessed Ramadan.
6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሊከናወን ጥቂት ሳምንታት ብቻ ቀርተውታል። ዜጎች የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጠበቃል። የሕገ መንግሥታችን አንቀጽ 38 ሁሉም ኢትዮጵያዊ የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዳለው ይደነግጋል። የሀገራችንን የነገ ዴሞክራሲ ለመወሰን፣ ዛሬ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ እናውጣ። ካርድ ለማውጣት ነገ አትበሉ፤ ነገ ከዛሬ ይጀምራል።

Filannoon marsaa 6ffaa adeemsifamuuf torban muraasa qofatu hafe. Lammiileen mirga dimookiraasii filachuusaaniitti fayyadamuun hirmaannaa ho’aa akka taasisan ni eegama. Heerri Mootummaa keewwatni 38 lammiileen Itoophiyaa hundi mirga filachuufi filatamuu akka qaban tumeera. Carraa dimokiraasii egeree biyya keenyaa murteessuuf har’a kaardii filannoo filattootaa haa baafannu. Kaardii filannoo borin baafadha hin jedhinaa, ka’umsi borii har’a.
How to Cut in iMovie