Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
114K subscribers
5.1K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
ለምግብ ዋስትና፣ ለስራ እድል ፈጠራ ብሎም ለአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት አዲስ እና ጠንካራ አለምአቀፍ የግብርና የፋይናንስ ሞዴል አስፈላጊ ነው። ይህ በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ወቅት አጽንዖት የሰጠሁት ቁልፍ ነጥብ ነው።

#ኢትዮጵያ ውስጥ ከፖሊሲ እና ስትራቴጂዎች ባለፈ የግብርና ልማትን ለማጎልበት አቅምን ማሳደግ፣ በምግብ ራስን መቻልን ማረጋገጥ ብሎም የአየር ንብረት ለውጥን የመዋጋት ዋና ዋና ግቦችን ይዘን በርካታ ጅምር ስራዎችን እየሰራን ነው።

A new and robust agricultural global financing model is essential for food security, job creation and economic growth. This is a key point I emphasized during the UN Food Systems Summit +2.

In #Ethiopia, beyond policies and strategies, we have been actively implementing numerous initiatives with the overarching goals of enhancing agricultural resilience, ensuring food self-sufficiency, and combating climate change.
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላደረጉልን አቀባበል እና ላካሄድነው ግልጽ ውይይት አመሰግናለሁ። ታሪካዊ ትሥሥራችንን መሠረት አድርገን ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን እና ኢኮኖሚያዊ ትብብራችንን ማሳደግ እንቀጥላለን።

My gratitude to President Vladimir Putin for the warm reception and candid discussions. With our historical ties as a basis, Ethiopia and Russia will continue enhancing bilateral relations and economic cooperation.
የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋን ዛሬ በጽሕፈት ቤታችን አግኝቼ ሰፊ ውይይት አድርገናል። የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የትብብር አድማስ በማስፋት ለኢኮኖሚ እድገታችን በኮንሴሽናል ፋይናንስ፣ በአለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በኩል ጠንካራ የኢንቨስትመንት ፋይናንስ አቅርቦት እና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችንን የሚደግፍ የዘለቀ አስተዋፅዖ ይኖረዋል።

Pleased to receive World Bank President Ajay Banga today. The World Bank will be instrumental to our economic growth in expanding its scope of partnership with Ethiopia through increased concessional financing, robust investment financing through IFC and support for our homegrown economic reform agenda.
ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህዎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ያስገኙ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ገንብታ ወደ ስራ አስገብታለች። የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮችንም ገንብተን በስራ ላይ እንገኛለን።

ከአለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ ጋር በመሆን ዛሬ ጠዋት በአንደኛው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በምርት ስራ ላይ ካሉ ኢንዱስትሪዎቻችን ሁለቱን አብረን ጎብኝተናል። ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም ያላት ሀገር ብቻ ሳትሆን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መዋእለ ነዋይ ለማፍሰስ ለሚሹ ሁሉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች ነው።

Ethiopia has built and operationalized 13 industry parks that have enabled full time employment for thousands. We have also built and operationalized agro-processing industry parks.

Together with World Bank President Ajay Banga we visited two industries actively producing in one of our nationwide industry parks. Ethiopia has great potential and is creating a conducive environment for more investments in various industries.
የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን ተቀብዬ አነጋግሪያለው። ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች:: በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ አቋምም አላት።

I welcome to #Ethiopia Hayashi Yoshimasa, Foreign Minister of Japan. Ethiopia attaches great importance to its relations with Japan and remains committed to cooperate on issues of mutual interest.
The Ultimate Guide to Microsoft Publisher