Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
114K subscribers
5.1K photos
253 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የከተማ መኖሪያ ቤት እጥረትን ለማቃለል የሚያደርጋቸውን ጥረቶች በማየቴ ደስተኛ ነኝ። በስድስት ወራት ውስጥ በ3 ሄክታር መሬት ላይ በ16 ሕንፃዎች 500 ቤቶችን በ3 ቢሊየን ብር ገንብተዋል። የከተማ የመኖሪያ ፍላጎትን ለማሟላት፣ መንግሥት እንደዚህ ያሉ ተቋማቶን ማጠናከሩን ይቀጥላል።

Pleased to see the progress of the Federal Housing Corporation’s efforts in addressing urban housing shortages. In six months 500 houses have been built in 16 blocks on 3 hectares of land at a cost of Birr 3 billion. The government will continue developing such facilities to meet urban housing needs.
የዛሬ ዐሥር ዓመት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ተወጥኖ ተጀመረ። ከብዙ የሥራ መዘግየትና መጓተት በኋላ፣ የዛሬ ሦስት ዓመት ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት ታልሞ ሥራው ቀጠለ። ከ 14 እስከ 17 ፎቅ ያሏቸውን 6 ሕንጻዎች ይዞ፣ በ7,550 ሜትር ስኴር መሬት ላይ ያረፈው አዲሱ የኢመደኤ ዋና መሥሪያ ቤት፣ የሰላም ሚኒስቴርን፣ የአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ ማዕከልን፣ የፋይንስ ኢንተሌጀንስ ማዕከልን ቢሮዎች ይዟል። ከመሠረተ ልማት በተጨማሪ፣ የኢመደኤ ዋና መሥሪያ ቤት መሪ አፍሪካዊ የሳይበር ተቋምን እውን የማድረግ ራእይን የያዘ ነው። ኢመደኤ በመላው ሀገሪቱ ያሉ ተቋማት ተምሳሌትነቱን ሊከተሉ የሚገባ ነው። ምንም ዓይነት ተግዳሮት ቢገጥመን፣ ሀገራዊ የብልጽግና ሕልማችን ሳይደናቀፍ ይቀጥላል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢመደኤ ዋና መስሪያቤት ምርቃት
INSA Headquarters Inauguration
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ ዓባይ ወንዝን ለልማቷ ስታውል፣ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት የማስከተል ፍላጎትም ዕቅድም የላትም። ባለፈው ዓመት የተገኘው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የሕዳሴውን ግድብ የመጀመሪያ ዙር ሙሌት እውን ያደረገ ሲሆን፣ የግድቡ መኖር በራሱ ጎረቤት ሀገራችን ሱዳን በጎርፍ እንዳትጥለቀለቅ በአስተማማኝ ሁኔታ ተከላክሎላታል። ኢትዮጵያ ሁለተኛው የውኃ ሙሌት ከመቀጠሉ በፊት፣ አዲስ በተጠናቀቁት የውኃ መውረጃዎች አማካኝነት ባለፈው ዓመት ከተገደበው ተጨማሪ ውኃን የምትለቅቅ ሲሆን፣ መረጃንም ታጋራለች። ሁለተኛው ሙሌት የሚከናወነው ከፍተኛ የዝናብ መጠን በሚገኝባቸው የሐምሌ/ነሐሴ ወራት በመሆኑ፣ ሱዳን በጎርፍ እንዳትጥለቀለቅ ለመከላከል ይጠቅማታል።

Ethiopia, in developing Abbay River for its needs, has no intention of causing harm to lower riparian countries. Heavy rains last year enabled successful first filling of the GERD while the presence of the GERD itself has undoubtedly prevented severe flooding in neighboring Sudan. Ahead of the second filling, Ethiopia is releasing more water from last year storage through newly completed outlets & sharing information. The next filling takes place only during heavy rainfall months of July/August, ensuring benefits in reducing floods in Sudan.
የትግራይ ክልልን መልሶ የመገንባት ሥራ የበርካታ አካላትን፣ በተለይም የክልሉ ተወላጆችን ተሳትፎ ይሻል። ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ የንግድ ተቋማት ባለቤቶች እና ምሁራን ጋር ተገናኝቼ በወቅታዊ ጉዳዮች እና በትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገናል።

Hojiin Naannoo Tigraay deebisanii ijaaruu hirmaannaa qaamolee hedduu keessaayyuu kan dhalattoota naannichaa barbaada. Har'a ganama abbootii dhaabbilee daldalaa dhalattoota Tigraay Finfinneetti jiraataniifi hayyoota waliin dhimmoota haala yeroofi haala Naannoo Tigraay irratti marii gooneerra.

Rebuilding the Tigray Region requires the concerted efforts of various actors, especially those from the region. I met this morning with business owners and scholars from the Tigray Region living in Addis Ababa, to discuss current issues and the situation in Tigray.
የ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሂደት ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ እንዲሆን በቁርጠኝነት እየሠራን ነው። ባለፈው ከክልል አመራሮች እና ከምርጫ ቦርድ ጋር ባካሄድነው ስብሰባ፣ ቀሪ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲከፈቱ እና ያልተጠናቀቁ ጉዳዮች እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ ማስቀመጣችን ይታወሳል። ዛሬ ቀጣይ ስብሰባ አካሂደን፣ ክንውኑን ገምግመናል። ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ አንዱ ማሳያ ሲሆን፣ ልዩነቶች በጥይት ሳይሆን በምርጫ ካርድ አማካኝነት የሚፈቱበት ነው። በምርጫ ሂደት፣ ዜጎች የተማመኑበትን በሙሉ ልብ ለመምረጥ እና ዴሞክራሲያዊ ሂደትን ለመገንባት ንቁ ተሳትፎ የማድረግ ዕድል ያገኛሉ። መጪው ምርጫ ኢትዮጵያን ወደ ፊት የሚያስፈነጥር እንደ መሆኑ፣ በጋራ የዜግነት ግዴታችንን መወጣት ያስፈልገናል። ነገን እንዲወስኑ፣ ዛሬ ይመዝገቡ!
The Art of Tweeting: Crafting Engaging and Shareable Content on Twitter