Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
113K subscribers
5.07K photos
249 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
የኢትዮጵያውያን ሕይወት ከዛፎች እና ከጫካ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው፡፡ ዛሬ የ2013ን የ #አረንጓዴዐሻራን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አስጀምረናል። በ2011 የአካባቢን ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ችግሮች ለመቅረፍ አስበን የአራት ዓመት ዕቅድ በማውጣት ያቀረብነው ሀገራዊ ጥሪ አንድ አካል ነው፡፡ በጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የምግብ ዋስትናን ያለማረጋገጥ፣ አካባቢ ተኮር ግጭቶች እና የመሳሰሉ አሉታዊ ሁኔታዎችን የመከላከያ መንገዱ በእጃችን ነው፡፡ ለመላው ኢትዮጵያውያን “ኢትዮጵያን እናልብሳት” ብዬ ጥሪ አቀርባለሁ። ጥሪው ሀገራችንን አረንጓዴ እናልብስ፣ በክልል ፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ በጾታ ከመከፋፈል አልፈን፣ ለዚህ ታላቅ ሕዝብ በሚመጥን መልኩ፣ ኢትዮጵያችንን በብልጽግና እና በክብር በአንድነት የተፈጥሮ ልብሷን እናልብሳት ማለቴ ነው።
ስኬት የትጋት ውጤት ነው። በ2011 #አረንጓዴዐሻራን ስናስጀምር በ4 ዓመታት ውስጥ 20 ቢልየን ችግኞችን ለመትከል ተነሣን። የ2013ን የተከላ ወቅት በምናጠናቅቅበት በዚህ ጊዜ፣ በ3 ዓመታት ውስጥ በአጠቃላዩ 18 ቢልየን ችግኞችን ተክለናል። በየምዕራፉ ከዓመታዊ ግባችን የበለጠ ውጤትን አስገኝተናል። #ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ አንድነትና መልካም ፈቃድ ላይ ተመርኩዛ በሌሎች መስኮችም የድል ጎዳናን ይዛ ትገሰግሳለች!

Success is an outcome of diligence. We launched #GreenLegacy in 2019 aiming for 20bil seedlings in 4 years. As we wind down 2021 planting season, our 3 year total achievement is 18bil planted. At each juncture we have exceeded annual set targets. #Ethiopia will continue on this success trajectory in other areas building on the unity and positive goodwill of its people!
ከሶስት ዓመታት በፊት የተተከሉት እነዚህ የቡና ዛፎች የ#አረንጓዴዐሻራን ፍሬ እያፈሩ ነው። የኢትዮጵያ #አረንጓዴዐሻራ መርሃ ግብር ስነ-ምህዳሩን ከማረጋጋት ባለፈ የግብርና ደን ልማትን በማጎልበት ላይ ይገኛል።

Hundeewwan bunaa waggaa sadii dura dhaabaman kunneen ija #AshaaraaMagariisaa godhataa Jiru. Sagantaan #AshaaraaMagariisaa Itoophiyaa sirna naannawaa uumamaa tasgabbeessuu irraa darbee qonna bosonarraa argamu gabbisuurratti argama.

These coffee trees planted three years ago as part of our #GreenLegacy are bearing fruit. Ethiopia’s #GreenLegacy program is not only stabilizing the ecosystem but also enhancing agroforestry.
The Best Dell Monitor for Your Needs