Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
✔
111K subscribers
4.85K photos
242 videos
63 links
ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!
Download Telegram
ብዙዎቹ የሙያ ዘርፎች ፍላጎትና ተሰጥኦ ይሻሉ። ለውትድርና ግን ቀዳሚው ጉዳይ ጥልቅ የሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት ነው። እንደ ሌላው ሙያ ውትድርና እውቀትና ጉልበት ብቻ አይፈልግም፤ ደምና አጥንትን ለመገበር ዝግጁ መሆን ጭምር እንጂ። ባንዴራችን የሚውለበለበው ከሁሉ በላይ ከጀግና ወታደሮቻችን በሚፈልቀው ትንፋሽ ነው። ታከተኝ ሳይሉ ሀገርን ከማገልገል፣ ሳይሰስቱ ፍቅርን ከመስጠት፣ በመርህ ኖሮ ለመርህ ከመሰዋት የበለጠ አኩሪ ገድል የለም። ሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ “የወታደር ልጅ ነኝ” ብላ ስትናገር እጅግ በኩራት ነው። ወታደር መሆን ደግሞ ኩራቱ የትናየት ከፍ እንደሚል አስቡት፡፡ ሳይሰስቱ ሀገር ማፍቀርንና ሳይታክቱ ሕዝብ ማገልገልን ከወታደሮቻችን እንማር!
ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ፈተና በድል ትሻገረዋለች። በድል የምትሻገረውን ኢትዮጵያ ለማልበስ አረንጓዴ ዐሻራችንን እናሳርፍ። ኢትዮጵያን ለማዳን እንዘምታለን፤ ኢትዮጵያን ለማልበስ እንተክላለን።
ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር ሩጫ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘቷ እንኳን ደስ አለን ማለት እወዳለሁ። ለቀሩት ተወዳዳሪዎቻችንም መልካም ዕድል እመኛለሁ ። ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች በማለፍ ድል ማስመዝገቧን ትቀጥላለች!

Olompikii Tokiyoo irratti Itoophiyaan warqee isa jalqabaa fiigicha meetira 10,000 tiin Salamoon Baaraggaatiin argachuusheetiin baga gammanne jechuun barbaada. Dorgomtoota hafaniifis carraa gaariin hawwa. Itoophiyaan qorumsa ishee mudate ceetee ilmaansheetiin injifannoo galmeessisuu itti fufti.
በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ቆራጥ ሴቶች እና ወንዶች ልጆችሽ አንቺን ለመታደግ ዘብ ቆመዋል! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

መልካም ምሽት ኢትዮጵያዬ!
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በወንዶች በ3000 ሜትር መሰናክል በለሜቻ ግርማ የብር ሜዳሊያ እንዲሁም በሴቶች 5ሺህ ሜትር ሩጫ በጉዳፍ ፀጋይ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘቷ እንኳን ደስ አለን። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ገና ከፍ ብላ ትደምቃለች።

Olompikii Tokiyoo irratti Itoophiyaan fiigicha gufachiisaa meetira 3000 warra dhiiraatiin Lammeechaa Girmaatiin medaaliyaa meetii,akkasumas fiigicha meetira 5000 warra dubaraatiin Gudaaf Tsaggaayeetiin medaaliyaa naasaa argachuusheetiin baga gammanne jechuun barbaada. Itoophiyaan carraaqqii ilmaansheetiin oljettee mul'achuu itti fufti.
#ኢትዮጵያ፦ ለሠራዊታችን ደም እንለግስ። የዐቅመ ደካሞችን ቤት እናድስ። #አረንጓዴዐሻራችንን እናሳርፍ። የግብርና ምርታማነታችንን በእጥፍ እናሳድግ። የየቢሮ ሥራችንን ዐቅምና ጊዜ ጨምረን እንሥራ፤ እያንዳንዳችን ከሚጠበቅብን በላይ ስንወጣ፣ ሁሉም ነገር ይስተካከላል!

#Ethiopia: Donate blood for the armed forces. Renovate the homes of those in need. Plant your #GreenLegacy print. Double down on agriculture productivity. When we each do our part, the whole comes together!
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በሴቶች 10,000 ሜትር ሩጫ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ የነሀስ ሜዳሊያ በማግኘቷ እንኳን ደስ አለን። ለቀሩት የወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻችን መልካም ዕድል እመኛለሁ፡፡

Olompikii Tokiyoo irratti Itoophiyaan fiigicha meetira 10,000 warra dubaraatiin atileet Lattasanbat Gideeyiin medaaliyaa naasaa argachuusheetiin baga gammanne jechuun barbaada. Dorgoomtoota maaraatooniiwarra dhiiraa hafaniif carraa gaariin hawwa.
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
The Benefits of Using a YT Audio to MP3 Converter